1 ቆሮንቶስ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሊሆን ከተጠራ ከጳውሎስና ከወንድማችን ከሶስቴንስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ እንዲሆን ከተጠራው ከጳውሎስ፣ ከወንድማችንም ከሶስቴንስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግዚአብሔር ጥሪና ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ጳውሎስ፥ ከወንድማችንም ሶስቴንስ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ለመሆን ከተጠራው ከጳውሎስና ከወንድማችንም ከሶስቴንስ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ ጳውሎስ ወንድሙም ሶስቴንስ፥ |
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ የመረጣችሁኝ አይደለም፤ እንድትሄዱ፥ ፍሬም እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም እንዲኖር፤ አብንም በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እንዲሰጣችሁ ሾምኋችሁ።
ጌታችን ኢየሱስም ዳግመኛ እንዲህ አላቸው፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እኔን እንደ ላከኝ እንዲሁ እኔ እናንተን እልካችኋለሁ።”
አረማውያንም ሁሉ የምኵራቡን አለቃ ሶስቴንስን ይዘው በሸንጎ ፊት ደበደቡት፤ የእርሱም ነገር ጋልዮስን ምንም አላሳዘነውም።
የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማስተማር ተለይቶ ከተጠራ ሐዋርያ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሚሆን ከጳውሎስ፥
ከሐዋርያት ሁሉ እኔ አንሣለሁና፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስለ አሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ፥
በእግዚአብሔር ሥራ እንተባበራለንና፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ጳውሎስና ከወንድማችን ጢሞቴዎስ በቆሮንቶስ ሀገር ላለችው የእግዚአሔር ቤተ ክርስቲያንና በአካይያ ሀገር ላሉ ቅዱሳን ሁሉ፥
እነርሱ አስቀድመው በፈቃዳቸው፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔርም፥ ለእኛም አሳልፈው ሰጥተዋልና እኛ እንደ አሰብነው አይደለም፤
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና ከሙታን ለይቶ በአስነሣው በእግዚአብሔር አብ ነው እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ሐዋርያ ካልሆነ ከጳውሎስ፥
በእግዚአብሔር ፈቃድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ከጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ በኤፌሶን ላሉ ቅዱሳን፥
እርሱም ጸጋን ሰጠ፤ ከቤተ ሰቦቹም ሐዋርያትን፥ ከእነርሱም ነቢያትንና የወንጌል ሰባኪዎችን፥ ጠባቂዎችንና መምህራንን ሾመ።