1 ዜና መዋዕል 16:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸው የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር አቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም “ፍቅሩ ለዘላለም ነውና” እያሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና እንዲያቀርቡ ኤማንና ኤዶታም እንዲሁም ተመርጠውና ስማቸው ተመዝግቦ የተመደቡ ሌሎችም ዐብረዋቸው ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና ጌታን እንዲያመሰግኑ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸውም የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር በዚያ ተዋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ከእነርሱ ጋር ሄማን፥ ይዱታን እንዲሁም የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ ፍቅር በማሰብ ዘወትር ለእርሱ የምስጋና መዝሙር ያቀርቡ ዘንድ ሌሎችም በተለይ የተመረጡ ሰዎች ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምሕረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸውም የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር አቆመ። |
ሌዋውያኑም የኢዩኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳንን ልጅ ኢታንን፥
ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፥ “ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚሉትንም፥ በቅድስና የሚያመሰግኑትን፥ ለእግዚአብሔርም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ።
መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑ በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ፥ “እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” እያሉ በአንድ ቃል ድምፃቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው በመለከትና በጸናጽል፥ በዜማም ዕቃ ሁሉ እግዚአብሔርን ባመሰገኑ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር የክብሩ ደመና የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ ድንጋይ በተነጠፈበትም ምድር በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፥ “እርሱ ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
ደግሞ፥ “ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና” እያሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ እርስ በርሳቸው ያስተዛዝሉ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቤት በተመሠረተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያከበሩ በታላቅ ድምፅ ዘመሩ።
ሌዋውያንንም እንዲያገለግሉ ዳዊትና አለቆቹ ከሰጡአቸው ናታኒም ውስጥ ሁለት መቶ ሃያ ናታኒምን አመጡ፤ እነዚህም ሁሉ በስም በስማቸው ተሰበሰቡ።
የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። የዚያችን ምድር ምርኮኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አገባኝ፤ እነሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፤ መግቢያውም ወደ ደቡብ ይመለከት ነበረ፤ ሌላውም ወደ ደቡብ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፤ መግቢያውም ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።