የሠራዊት እምላክ ስለሚነግሥ ጨረቃ ትጨልማለች፥ ፀሐይም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ እርሱ በኢየሩሳሌም፥ በጽዮን ተራራ ላይ ሆኖ ያስተዳድራል፤ የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ ክብሩን ያያሉ።
ራእይ 6:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለከትኩ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይ እንደ ጥቊር የሐዘን ልብስ ጠቈረች፤ ጨረቃም በሙሉ እንደ ደም ቀላች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድስተኛውን ማኅተም ሲፈታ ተመለከትሁ፤ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሓይም እንደ ማቅ ጠቈረች፤ ጨረቃም በሙሉ እንደ ደም ቀላች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጉር ጥቁር ሆነች፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፥ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፥ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፥ |
የሠራዊት እምላክ ስለሚነግሥ ጨረቃ ትጨልማለች፥ ፀሐይም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ እርሱ በኢየሩሳሌም፥ በጽዮን ተራራ ላይ ሆኖ ያስተዳድራል፤ የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ ክብሩን ያያሉ።
የሠራዊት ጌታ አምላክ ነጐድጓድን፥ የመሬት መናወጥን፥ ታላቅ ድምፅን፥ ዐውሎ ነፋስን፥ ሞገድንና የሚባላ የእሳት ነበልባልን በጠላቶችሽ ላይ በመላክ አንቺን ይታደግሻል።
ፀሐይ፥ ጨረቃና ከዋክብት ሁሉ ይጠፋሉ፤ ሰማይም እንደ ብራና ተጠቅሎ ይወገዳል፤ ከዋክብትም እንደ ወይንና እንደ በለስ ዛፍ ቅጠል ይረግፋሉ።
ዖዝያን በይሁዳ፥ የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓምም በእስራኤል ላይ በነገሡበት ዘመን፥ በተቆዓ ከሚገኙ እረኞች አንዱ የሆነው አሞጽ የምድር መናወጥ ከመሆኑ ሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል የተናገረው የትንቢት ቃል ይህ ነው።
እናንተም ተራራውን በሁለት ከፍሎ እስከ አጻል በደረሰው በዚህ ሸለቆ ውስጥ አልፋችሁ ታመልጣላችሁ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ምድር በተናወጠች ጊዜ የቀድሞ አባቶቻችሁ በሸሹት ዐይነት ትሸሻላችሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬም ቅዱሳኑን አስከትሎ ይመጣል።
“ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ተአምራት፥ በጢሮስና በሲዶና ከተሞች ተደርገው ቢሆን ኖሮ በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የሐዘን ልብስ ለብሰውና ዐመድ በላያቸው ላይ ነስንሰው ገና ዱሮ ንስሓ በገቡ ነበር!
“ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ።
የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውንም ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ!” አሉ።
በዚያኑ ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማይቱም አንድ ዐሥረኛ ፈራረሰ፤ በምድር መናወጥም ምክንያት ሰባት ሺህ ሰዎች ሞቱ፤ ከሞት የተረፉትም እጅግ ፈሩ፤ የሰማይንም አምላክ አከበሩ።
መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ይህን የመሰለ ታላቅ የምድር መናወጥ ሰው በምድር ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ ሆኖ አያውቅም።
አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፥ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ፥ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛቸው ጨለመ፤ በዚህ ዐይነት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛ ያለ ብርሃን ሆነ።