መዝሙር 96:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዙሪያው ያለው ክብርና ግርማ ነው፤ ኀይልና ውበትም በመቅደሱ ውስጥ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው፤ ብርታትና ክብርም በመቅደሱ ውስጥ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ውበት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ። |
እግዚአብሔርን አንድ ነገር እለምነዋለሁ፤ የምለምነውም፦ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ የእግዚአብሔርን አስደናቂነት እንድመለከትና በቤተ መቅደሱም መጸለይ እንድችል ነው።
የእግዚአብሔር ድምፅ አጋዘንን እንድትወልድ ያደርጋል የዛፎችን ቅጠል ያረግፋል፤ በመቅደሱም ያሉ ድምፁን ሲሰሙ “ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” ይላሉ።
እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ትክክል ነው። በኀያል ቃሉ ዓለምን ሁሉ ደግፎ ይዞአል፤ ሰዎችንም ከኃጢአት ካነጻ በኋላ በሰማይ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦአል።