በዚህ ዐይነት መላው እስራኤላውያን ጥሩምባና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽል እያንሿሹ፥ መሰንቆና በገና እየደረደሩ በሆታና በእልልታ የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
መዝሙር 47:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ! ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤ ንጉሣችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክ በእልልታ፥ ጌታ በመለከት ድምፅ ዐረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንቀጥቀጥም ያዛቸው፥ እንደ ወላድም በዚያ አማጡ። |
በዚህ ዐይነት መላው እስራኤላውያን ጥሩምባና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽል እያንሿሹ፥ መሰንቆና በገና እየደረደሩ በሆታና በእልልታ የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ከዚህ በኋላ ዳዊት ሕዝቡን “አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ!” አለ፤ መላው ጉባኤም የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ወደ መሬት ለጥ ብለውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ለንጉሡም ክብር ሰጡ።
ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፤ በደመናዎች ላይ ለሚጓዘው መንገድ አዘጋጁ፤ ስሙ እግዚአብሔር ነው፤ በፊቱ ደስ ይበላችሁ!
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!