ንጉሥ አክዓብ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ፥ ቤተ መንግሥቱን በዝሆን ጥርስ እንዴት አስጊጦ እንደ ሰራውና የሠራቸውም ከተሞች ሁኔታ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።
መዝሙር 45:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከከርቤ፥ ከእሬትና ከብርጒድ የተቀመመ ሽቶ በንጉሣዊ ልብስህ ላይ ተርከፍክፎአል፤ በዝሆን ጥርስ በተጌጠው ቤተ መንግሥትህም የበገና ሙዚቃ ቃና ያስደስትሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልብስህ ሁሉ በከርቤ፣ በአደስና በጥንጁት መዐዛ ያውዳል፤ በዝኆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶችም፣ የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኙሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፥ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተአምራት እንድታዩ ኑ። |
ንጉሥ አክዓብ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ፥ ቤተ መንግሥቱን በዝሆን ጥርስ እንዴት አስጊጦ እንደ ሰራውና የሠራቸውም ከተሞች ሁኔታ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።
እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ! እነሆ ወደ አትክልት ቦታዬ ገባሁ፤ ከርቤዬንና የሽቶ አበባዎቼን ለቀምኩ፤ የማር ሰፈፌን ከወለላው ጋር ተመገብኩ፤ የወይን ጠጄንና ወተቴንም ጠጣሁ። ወዳጆቼ ሆይ! በፍቅር እስክትረኩ ድረስ ብሉ፥ ጠጡ።
የጉንጮቹ ማማር ጣፋጭ ሽታ ያላቸው የቅመማቅመም ዕፀዋት እንደሚገኙበት የአትክልት ቦታ ነው፤ ከንፈሮቹ መዓዛው የሚጣፍጥ የከርቤ ሽቶ እንደሚያፈሱ የአሸንድዬ አበባዎች ናቸው።
የክረምቱንና የበጋውን ወራት የሚያሳልፉባቸውን ቤቶች ሁሉ እደመስሳለሁ፤ በዝሆን ጥርስ አጊጠው የተሠሩ ቤቶች ሁሉ ይፈርሳሉ፤ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ይወድማሉ።”
ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር ሆኖ አዩት፤ ተደፍተውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው የወርቅ፥ የዕጣንና የከርቤ ስጦታ አቀረቡለት።
የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ።