መዝሙር 24:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከአዳኝ አምላኩ ከእግዚአብሔር በረከትንና ፍትሕን ይቀበላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ በረከትን ከእግዚአብሔር ዘንድ፣ ጽድቅንም ከአዳኝ አምላኩ ይቀበላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ከጌታ ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ጽድቅን ይቀበላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤ አንተ አምላኪዬና መድኀኒቴ ነህና፥ ዘወትርም አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና። |
የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤ ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤ እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።
በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።
እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከእግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ዘለዓለማዊ ደኅንነት ትድናላችሁ፤ ለዘለዓለምም ኀፍረትና ውርደት ከቶ አይደርስባችሁም።
እነርሱ ብል እንደ በላው ልብስና ትል እንደበላው ሱፍ ይሆናሉ፤ የእኔ ታዳጊነት ግን ዘለዓለማዊ ነው፤ አዳኝነቴም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።”
አንቺን ለማጥፋት የሚሠራ መሣሪያ ዘላቂነት አይኖረውም፤ ለሚከሱሽ ሁሉ በቂ መልስ ይኖርሻል፤ የእኔ አገልጋዮች ርስትና ከእኔ የሚፈረድላቸው ፍርድ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
ይህም የሆነው እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው በረከት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ለአሕዛብ እንዲደርስና እኛም እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያለውን መንፈስ ቅዱስን በእምነት እንድንቀበል ነው።
ይህንንም የማደርግበት ምክንያት በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴን ጽድቅ ትቼ በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ በክርስቶስ በማመን ለማግኘትና ከእርሱም ጋር ለመሆን ነው።