Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 24:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እርሱ በረከትን ከእግዚአብሔር ዘንድ፣ ጽድቅንም ከአዳኝ አምላኩ ይቀበላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እርሱ ከጌታ ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ጽድቅን ይቀበላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከአዳኝ አምላኩ ከእግዚአብሔር በረከትንና ፍትሕን ይቀበላል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በእ​ው​ነ​ትህ ምራኝ፤ አስ​ተ​ም​ረ​ኝም፤ አንተ አም​ላ​ኪ​ዬና መድ​ኀ​ኒቴ ነህና፥ ዘወ​ት​ርም አን​ተን ተስፋ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 24:5
31 Referencias Cruzadas  

ሕግ በመጠበቅ የሚገኝ የራሴ ጽድቅ ኖሮኝ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚመጣ፣ ከእምነትም በሆነ ጽድቅ በርሱ ዘንድ እንድገኝ ነው።


በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤


ጽድቄን እያመጣሁ ነው፤ ሩቅም አይደለም፤ ማዳኔም አይዘገይም። ለጽዮን ድነትን፣ ለእስራኤል ክብሬን አጐናጽፋለሁ።


ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች እያደረጋችሁ በረከትን ለመውረስ ነው።


ለአብርሃም የተሰጠው በረከት፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ለአሕዛብ እንዲደርስ ዋጅቶናል፤ ይኸውም በእምነት የመንፈስን ተስፋ እንድንቀበል ነው።


እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ድነቴም ሆኗል።”


የምስጋናን መሥዋዕት የሚሠዋ ያከብረኛል፤ መንገዱንም ቀና ለሚያደርግ፣ የእግዚአብሔርን ማዳን አሳየዋለሁ።”


እኛ ግን ተስፋ የምናደርገውን ጽድቅ፣ በመንፈስ አማካይነት በእምነት ሆነን በናፍቆት እንጠባበቃለን።


ስለዚህ በእምነት የሆኑት፣ የእምነት ሰው ከሆነው ከአብርሃም ጋራ ቡሩካን ናቸው።


እኛ በርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።


በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከርሱ የተነሣ ነው፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፣ ጽድቃችንና ቅድስናችን፣ ቤዛችንም ሆኗል።


ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው። ልዩነት የለም፤


ማንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ ቢፈልግ፣ የእኔ ትምህርት ከእግዚአብሔር ወይም ከራሴ የመጣ መሆኑን ለይቶ ያውቃል፤


በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፤ ነፍሴ በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች፤ ሙሽራ ራሱን እንደሚያሳምር፣ ሙሽራዪቱም በዕንቈቿ እንደምታጌጥ፣ የድነትን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።


በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤ የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።


ብል እንደ ልብስ ይበላቸዋል፤ ትል እንደ በግ ጠጕር ይውጣቸዋል፤ ጽድቄ ግን ለዘላለም፣ ማዳኔም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንታ ትኖራለች።”


እስራኤል ግን በእግዚአብሔር፣ በዘላለም ድነት ይድናል፤ እናንተም ለዘላለም፣ አታፍሩም፤ አትዋረዱም።


አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በቀንና በሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ።


ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ ዝናው ፀሓይ የምትኖረውን ዘመን ያህል ይዝለቅ። ሕዝቦች ሁሉ በርሱ ይባረኩ፤ ሕዝቡ ሁሉ ቡሩክ ነህ ይበለው።


ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣ አዳኝ አምላካችን፣ ጌታ ይባረክ። ሴላ


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios