በማግስቱ ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሣ፤ ጥቂት ምግብ፥ ውሃም በአቁማዳ ሞልቶ ለአጋር ሰጣት፤ ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም ከዚያ ወጥታ በቤርሳቤህ በረሓ ትንከራተት ጀመር።
ምሳሌ 27:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቤቱ ርቆ የሚሄድ ሰው ከጎጆዋ ርቃ እንደምትበር ወፍ ተንከራታች ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣ ጐጆዋን ለቅቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቦታው ርቆ የሚሄድ ሰው ከጎጆዋ ርቃ እንደምትበርር ወፍ ነው። |
በማግስቱ ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሣ፤ ጥቂት ምግብ፥ ውሃም በአቁማዳ ሞልቶ ለአጋር ሰጣት፤ ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም ከዚያ ወጥታ በቤርሳቤህ በረሓ ትንከራተት ጀመር።
ንጉሡም “ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ ያሰብከው ከቶ ምን ተጓድሎብህ ነው?” አለው። ሀዳድም “ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ” ሲል ለንጉሡ መለሰ፤
የአርኖንን ወንዝ የሚሻገሩ የሞአብ ሴቶች ከጎጆዎቻቸው ተበታትነው ክንፎቻቸውን እያራገቡ ወዲያና ወዲህ እንደሚንከራተቱ የወፍ መንጋዎች ናቸው።
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ለመኰብለል አስቦ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወርዶ ከዚያ ወደ ተርሴስ የምትጓዝ መርከብ አገኘ፤ ለጒዞ የሚያስፈልገውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ ወደ መርከቢቱ ገባ፤ ሐሳቡም ከእግዚአብሔር ለመሸሽ ነበር።
የአሳፋሪ ድርጊታቸውን ዐረፋ የሚደፍቁ፥ እንደ ተቈጣ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም እንደሚጠብቃቸውና፥ እንደሚንከራተቱ ኮከቦች ናቸው።
ከዚህ በኋላ ነቢዩ ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ “በዚህ አትቈይ፤ አሁኑኑ ፈጥነህ ወደ ይሁዳ ሂድ” ሲል ነገረው፤ ስለዚህም ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ።