Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 22:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚህ በኋላ ነቢዩ ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ “በዚህ አትቈይ፤ አሁኑኑ ፈጥነህ ወደ ይሁዳ ሂድ” ሲል ነገረው፤ ስለዚህም ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ይሁን እንጂ ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፣ “በዐምባው ውስጥ አትቈይ፤ ሂድና ወደ ይሁዳ ምድር ግባ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ይሁን እንጂ ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፥ “በዐምባው ውስጥ አትቆይ፤ ሂድና ወደ ይሁዳ ምድር ግባ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ነቢዩ ጋድም ዳዊ​ትን፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ እንጂ በአ​ን​ባው ውስጥ አት​ቀ​መጥ” አለው፤ ዳዊ​ትም ሄደ፤ ወደ ሳሬቅ ከተ​ማም መጥቶ ተቀ​መጠ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ነቢዩ ጋድም ዳዊትን፦ ተነሥተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ እንጂ በአምባው ውስጥ አትቀመጥ አለው፥ ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ሔሬት ዱር መጣ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 22:5
8 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ሕዝቅያስ እግዚአብሔር በነቢዩ ጋድና በነቢዩ ናታን አማካይነት ለንጉሥ ዳዊት የሰጠውንና ዳዊትም ተግባራዊ ያደረገውን ትእዛዝ በመከተል በበገና፥ በጸናጽልና በመሰንቆ የሠለጠኑ ሌዋውያንን በቤተ መቅደሱ ውስጥ መደበ፤


ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያለው የንጉሥ ዳዊት ታሪክ ሳሙኤል፥ ናታንና ጋድ ተብለው በሚጠሩት ሦስት ነቢያት በጻፉአቸው የታሪክ መጻሕፍት ተመዝግቦ ይገኛል፤


በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የዳዊት ነቢይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤


እግዚአብሔርም የዳዊትን ነቢይ ጋድን “ሄደህ ዳዊትን ‘እነሆ ሦስት ምርጫ ሰጥቼሃለሁ፤ እኔም አንተ የምትመርጠውን አደርግብሃለሁ’ ይላል” ብለህ ንገረው። በማግስቱ ጠዋት ዳዊት ከእንቅልፉ ከተነሣ በኋላ፥


በዚህም ዐይነት ወላጆቹን በሞአብ ንጉሥ ዘንድ ተዋቸው፤ እነርሱም ዳዊት እየተደበቀ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ በዚያው ቈዩ።


ዳዊት በዚያን ጊዜ በተመሸገ ኮረብታ ላይ ነበር፤ ከፍልስጥኤማውያን ሠራዊት አንድ ቡድን ቤተልሔምን በመውረር ያዘ፤


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች።


ዳዊት በዚያን ጊዜ፥ በተመሸገ ኰረብታ ላይ ነበር፤ ከፍልስጥኤማውያን ሠራዊት አንዱ ቡድን ቤተልሔምን በመውረር ያዘ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios