ምሳሌ 24:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ዘወትር በአእምሮአቸው ግፍን ያቅዳሉ፤ በአንደበታቸውም ይሸነግላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልባቸው ዐመፅን ያውጠነጥናልና፤ ከንፈራቸውም ሸፍጥ ያወራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልባቸው ግፍን ታስባለችና፥ ከንፈራቸውም ተንኮልን ትናገራለችና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባቸው ሐሰትን ይማራልና። ከንፈራቸውም ምቀኝነትን ይናገራልና። |
ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ ቃል ይህ ነው፦ “እናንተ ማስጠንቀቂያን ንቃችሁ ይደግፈናል ብላችሁ በተማመናችሁበት በግፍና በማታለል ላይ እምነታችሁን ጥላችኋል።
ማንም ሰው ክስ ሲመሠርት ትክክለኛውን ጉዳይ ይዞ አይመጣም ወደ ፍርድ ሸንጎም ሲቀርብ ለሕግ ታማኝ ሆኖ አይደለም፤ እነርሱ ከንቱ በሆነ አቤቱታ ላይ ተመሥርተው ውሸትን ይናገራሉ፤ ተንኰልን አስበው በደልን ይፈጽማሉ።
እጆቻቸው ክፉ ነገርን ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ባለ ሥልጣኑና ዳኛው ጉቦ ይጠይቃሉ፤ ኀይለኛ ፍላጎቱን በግዴታ ተግባራዊ ያስደርጋል፤ በዚህም ዐይነት ሁሉም ፍርድን ያጣምማሉ።