ምሳሌ 21:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመዋሸት የሚገኝ ሀብት ተኖ እንደሚጠፋ እንፋሎትና እንደሚገድል ወጥመድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣ በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሐሰተኛ ምላስ መዝገብ ማከማቸት የሚበንን ጉም ነው፥ ይህን የሚፈልጉ ሞትን ይፈልጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሐሰተኛ ምላስ ሀብትን የሚያከማች ከንቱ ነገርን ይከተላል፥ ወደ ሞት ወጥመድም ያደርሰዋል። |
ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ሀብትን የሚሰበስብ፥ ያልጣለችውን ዕንቊላል ታቅፋ እንደምትፈለፍል ቆቅ ነው፤ በዕድሜው አጋማሽ የሰበሰበውን ሃብት ሁሉ ያጣል። በመጨረሻም ሞኝነቱ ግልጥ ይሆናል።
እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ፍርድ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!