ምሳሌ 10:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጻድቅ ሰው መታሰቢያ ለበረከት ይሆናል የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቃን መታሰቢያቸው በረከት ነው፤ የክፉዎች ስም ግን እንደ ጠፋ ይቀራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፥ የክፉ ስም ግን ይጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል። |
እርሱ ለእስራኤል ሕዝብ፥ ለእግዚአብሔርና ለቤተ መቅደሱ ስለ ሰጠው አገልግሎት ውለታ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መካነ መቃብር ቀበሩት።
ሕዝቅያስ ሞተ፤ በላይኛው ክፍል በሚገኘውም በዳዊት ልጆች መካነ መቃብር ተቀበረ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብም ሁሉ ታላቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት አደረጉለት፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ምናሴ ነገሠ።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል “በባቢሎን ላይ አደጋ ጥዬ አፈራርሳታለሁ፤ ምንም ነገር አላስቀርላትም፤ ለዘር እንኳ የሚተርፍ ትውልድ አይኖራትም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የእስራኤል ተስፋ ነህ፤ አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ፤ የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆንከውን አንተን እግዚአብሔርን ስለ ተዉ በትቢያ ላይ እንደ ተጻፈ ስም ይደመሰሳሉ።