Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 24:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እርሱ ለእስራኤል ሕዝብ፥ ለእግዚአብሔርና ለቤተ መቅደሱ ስለ ሰጠው አገልግሎት ውለታ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መካነ መቃብር ቀበሩት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እርሱም በእስራኤል ውስጥ ለእግዚአብሔርና ለቤተ መቅደሱ መልካም ሠርቷልና በዳዊት ከተማ በነገሥታቱ መቃብር ተቀበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በእስራኤልም፥ ለጌታና ለቤቱም ቸርነትን ሠርቶአልና በዳዊት ከተማ ከነገሥታቱ ጋር ቀበሩት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከቤ​ቱም ጋር መል​ካም ሠር​ቶ​አ​ልና በዳ​ዊት ከተማ ከነ​ገ​ሥ​ታቱ ጋር ቀበ​ሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከእስራኤልም ጋር፥ ከእግዚአብሔርና ከቤቱም ጋር ቸርነትን ሠርቶአልና በዳዊት ከተማ ከነገሥታቱ ጋር ቀበሩት።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 24:16
13 Referencias Cruzadas  

ዳዊት ሞተ፤ የእርሱ ከተማ በሆነችው በኢየሩሳሌምም ተቀበረ፤


ስለዚህም ኢዮአስ ዮዳሄንና ሌሎቹንም ካህናት ወደ እርሱ ጠርቶ “ቤተ መቅደሱን ያላደሳችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? ከዛሬ ጀምሮ የምትቀበሉትን ገንዘብ መያዝ የለባችሁም፤ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ይውል ዘንድ ገንዘቡን አስረክቡ” አላቸው።


የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሣፍጥ ልጅ የሆነው ኢዮራም ስድስት ወንድሞች ነበሩት፤ እነርሱም ዐዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዐዛርያ፥ ሚካኤልና ሸፋጥያ ተብለው የሚጠሩ ናቸው።


ኢዮራም በሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ስምንት ዓመት ገዛ፤ እርሱ በሞተ ጊዜ ማንም አላዘነለትም፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ይሁን እንጂ በነገሥታት መካነ መቃብር አልተቀበረም።


ዮዳሄ በዕድሜ እጅግ ከሸመገለ በኋላ በአንድ መቶ ሠላሳ ዓመቱ ሞተ፤


ዮዳሄ ከሞተ በኋላ ግን የይሁዳ መሪዎች ወደ ንጉሥ ኢዮአስ መጥተው እጅ በመንሣት ፍላጎታቸውን ገለጡለት፤ እርሱም በሐሳቡ ተስማማ፤


ንጉሥ ሕዝቅያስ በመላው የይሁዳ ግዛት መልካም የሆነውንና ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ አደረገ፤


አምላኬ ሆይ፥ ለቤተ መቅደስህና ለአገልግሎቱ መቃናት ስል እነዚህን ሁሉ በታማኝነት ማድረጌን በማሰብ ቸርነት አድርግልኝ።


የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ይህን በሰሙ ጊዜ መጡና በድኑን ወስደው ቀበሩት።


“ወንድሞቼ ሆይ! ከቀድሞ አባቶች አንዱ የሆነው ዳዊት እንደ ሞተና እንደ ተቀበረ፥ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ እንዳለ በግልጥ ልንገራችሁ።


እግዚአብሔር ቅን ፈራጅ ነው፤ ስለዚህ ሥራችሁንና በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን በመርዳት ስለ ስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የአንተ ቤተሰብና የቀድሞ አባትህ ቤተሰብ ለዘለዓለም ያገለግሉኝ ዘንድ ቃል ገብቼ ነበር፤ አሁን ግን እንዲህ አይሆንም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ የሚንቁኝም ይናቃሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos