ዘኍል 27:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ብቻ የአባታችን ስም ከእስራኤል ተፍቆ መጥፋት ይገባዋልን? ስለዚህ በአባታችን ዘመዶች መካከል ለእኛ የሚገባንን የርስት ድርሻ ስጡን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ አባታችን ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ስሙ ከጐሣዎቹ ተለይቶ እንዴት ይጠፋል? ለእኛም በአባታችን ዘመዶች መካከል ርስት ስጡን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድ ልጅስ ባይኖረው የአባታችን ስም ከወገኑ መካከል ለምን ይጠፋል? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስትን ስጠን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድ ልጅስ ባይኖረው የአባታችን ስም ከወገኑ መካከል ለምን ይጠፋል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድ ልጅስ ባይኖረው የአባታችን ስም ከወገኑ መካከል ለምን ይጠፋል? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስትን ስጠን አሉ። |
ሙሴ ግን እግዚአብሔር አምላኩን በመማለድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ በሥልጣንህና በታላቅ ኀይልህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸውን ሕዝብህን እስከዚህ የምትቈጣው ስለምነው?
“አባታችን አንድ እንኳ ወንድ ልጅ ሳይወልድ በምድረ በዳ ሞተ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋር ተባባሪ አልነበረም፤ የሞተውም በራሱ ኃጢአት ምክንያት ነው፤
እነርሱም ወደ ካህኑ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ መሪዎቹ ቀርበው “እንደ ወንዶች ዘመዶቻችን የርስት ድርሻ እንዲሰጠን እግዚአብሔር ሙሴን አዞታል” አሉአቸው። ስለዚህም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለእነርሱ ከወንዶች ዘመዶቻቸው ጋር የርስት ድርሻ ተሰጣቸው፤