ሉቃስ 9:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተስ፥ “እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፤ ጴጥሮስም፥ “አንተ የእግዚአብሔር መሲሕ ነህ፤” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “እናንተስ ማን ነው ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም፣ “አንተ የእግዚአብሔር ክርስቶስ ነህ” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ “የእግዚአብሔር መሢሕ ነህ፤” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው፤ ጴጥሮስም መልሶ፥ “አንተ የእግዚአብሔር መሲሕ ነህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ አለ። |
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። የካህናት አለቃውም እንደገና ኢየሱስን “በሕያው እግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሲሕ እንደ ሆንክ ንገረን!” አለው።
ኢየሱስ ግን ዝም አለ እንጂ ምንም መልስ አልሰጠም። የካህናት አለቃውም “የቡሩክ እግዚአብሔር ልጅ መሲሕ አንተ ነህን?” ሲል እንደገና ጠየቀው።
እነርሱም “አንዳንዶች ‘አጥማቂው ዮሐንስ ነው፤’ ሌሎች ‘ኤልያስ ነው፤’ ይሉሃል፤ ‘ከቀድሞዎቹ ነቢያት አንዱ ከሞት ተነሥቶአል፥’ የሚሉም አሉ፤” ብለው መለሱለት።
ሴትዮዋንም “ከእንግዲህ ወዲህ እርሱን የምናምነው አንቺ በነገርሽን ቃል ብቻ ሳይሆን እኛ ራሳችን ስለ ሰማንና በእርግጥ እርሱ የዓለም አዳኝ እንደ ሆነ ስላወቅን ነው” አሉአት።