ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
ዘሌዋውያን 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጁን በጠቦቱ ራስ ላይ ጭኖ በድንኳኑ ደጃፍ ፊት ለፊት ይረደው፤ ካህናቱም ደሙን በመሠዊያው ዙሪያ ይርጩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመሥዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጁንም ለቁርባን ባቀረበው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፥ በመገናኛውም ድንኳን ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጁንም ለቍርባን በቀረበው ራስ ላይ ይጭናል በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ያርደዋል፤ ካህናቱም የአሮን ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጁንም ለቍርባን በቀረበው ራስ ላይ ይጭናል፥ በመገናኛው ድንኳን ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። |
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
እርሱንም ከመሠዊያው በስተ ሰሜን በኩል በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ የአሮን ዘር የሆኑ ካህናትም ደሙን ወስደው በመሠዊያው ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።
ያ ሰው ወይፈኑን በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ትውልዳቸው ከአሮን ወገን የሆነ ካህናት ደሙን ወደ እግዚአብሔር ያቅርቡት፤ በድንኳኑ በር መግቢያ በኩል በሚገኘው መሠዊያ ጐኖች ሁሉ ላይ ይርጩት።
እጁንም በፍየሉ ራስ ላይ ጭኖ፥ ከመሠዊያው በስተ ሰሜን በኩል ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ስፍራ በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይረደው፤ ይህም ኃጢአትን የሚያስወግድ መሥዋዕት ይሆናል።
ይህም እግዚአብሔር በክርስቶስ የዓለምን ሰዎች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ ማለት ነው፤ በደላቸውንም አልቈጠረባቸውም፤ ለእኛም ሰውን ከጌታ ጋር የምናስታርቅበትን ቃል ሰጠን።