በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በስተደቡብ፥ አምስቱ ደግሞ በስተ ሰሜን የሚቀመጡት ዐሥሩ የወርቅ መቅረዞች፥ አበባዎች፥ የመብራት ቀንዲሎች፥ የእሳት መቈስቈሻዎች፥
ዘሌዋውያን 24:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮን መብራቶቹን በንጹሕ የወርቅ መቅረዝ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ባለሟቋረጥ የሚበሩ መሆናቸውንም ይቈጣጠራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ፊት በንጹሕ የወርቅ መቅረዝ ላይ ያሉት መብራቶች ያለ ማቋረጥ መሰናዳት አለባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ፊት በንጹሕ የወርቅ መቅረዝ ላይ መብራቶቹን ሁልጊዜ ያዘጋጃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ መቅረዝ ላይ መብራቶቹን ሁል ጊዜ እስኪነጋ አብሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ፊት በጥሩ መቅረዝ ላይ መብራቶቹን ሁልጊዜ ያሰናዳቸው። |
በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በስተደቡብ፥ አምስቱ ደግሞ በስተ ሰሜን የሚቀመጡት ዐሥሩ የወርቅ መቅረዞች፥ አበባዎች፥ የመብራት ቀንዲሎች፥ የእሳት መቈስቈሻዎች፥
የቤተ መቅደሱን በር ሁሉ ዘጉ፤ መብራቶቹንም አጠፉ፤ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ዕጣንን ማጠን ወይም የሚቃጠል መሥዋዕትን ማቅረብ ተዉ፤
የክብር ዘቡ አዛዥ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ የዕጣን ማጠኛዎችን፥ ጐድጓዳ ወጭቶችን፥ ድስቶችን፥ መቅረዞችን፥ ጭልፋዎችን፥ የመጠጥ መሥዋዕት ማቅረቢያዎችን፥ በወርቅና በብር የተሠሩ ዕቃዎችን ሁሉ ወሰደ።
አሮን በየምሽቱ መብራቱን ያቀጣጥላል፤ እርሱም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ባለው በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ካለው መጋረጃ ውጪ በእግዚአብሔር ፊት እስከ ንጋት ድረስ ሲበራ ያድራል፤ ይህም ድንጋጌ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ተጠብቆ ይኖራል።
የእነርሱም ኀላፊነት በቃል ኪዳኑ ታቦት፥ በገበታው፥ በመቅረዙ፥ በመሠዊያዎቹ፥ ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ በሚገለገሉባቸው ንዋያተ ቅድሳት፥ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በሚያስገባው መጋረጃ ላይ ሲሆን፥ በአጠቃላይ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት አገልግሎት ኀላፊነቱ የእነርሱ ነበር።
ሁለት ክፍሎች ያሉአት ድንኳን ተዘጋጅታ ነበር። መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት የነበረባት መጀመሪያይቱ ክፍል “ቅድስት” ትባል ነበር።
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ኮከቦችና የሰባቱም የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ኮከቦች የሰባቱ አብያተ ክርስቲያን መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞችም ሰባት አብያተ ክርስቲያን ናቸው።”
ከምን ያኽል ከፍተኛ ቦታ ላይ መውደቅህን አስታውስ! ንስሓም ግባ! በመጀመሪያ ታደርገው የነበረውን ሥራህን አድርግ፤ ይህን ሁሉ ባታደርግ ግን ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ንስሓም ካልገባህ መቅረዝህን ከስፍራው አነሣዋለሁ።