ኢያሱ 15:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ከታናናሽ ከተሞችዋና መንደሮችዋ ጋር ዔቅሮን የምትባል ከተማ ነበረች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቃሮን በዙሪያዋ ካሉ ሰፈሮችና መንደሮቿ ጋራ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቃሮን ከተመሸጉና ካልተመሸጉ መንደሮችዋ ጋር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቃሮን ከመንደሮችዋና ከመሰማሪያዎችዋ ጋር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቃሮን ከተመሸጉና ካልተመሸጉ መንደሮችዋ ጋር፥ |
ጋዛ ተለቃ ሰው የማይኖርባት ትሆናለች፤ አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች፤ የአሽዶድ ነዋሪዎች በቀትር ከመኖሪያቸው ይባረራሉ፤ የዓቃሮንም ሰዎች ከከተማይቱ ተፈናቅለው ይወጣሉ።
እነዚህም ከግብጽ በስተ ምሥራቅ ካለው ከሺሆን ወንዝ ጀምሮ ወደ ሰሜን እስከ ኤክሮን ድንበር ድረስ ያለው ነው። ይህም በአጠቃላይ ከነዓን ተብሎ ይጠራል። እርሱም የአምስቱ የፍልስጥኤም ማለት የጋዛ፥ የአሽዶድ፥ የአስቀሎና፥ የጋትና የኤክሮን ነገሥታት ግዛት ነው። ሌሎች ያልተያዙ ደግሞ በደቡብ በኩል ያለው የአቢብ ግዛት ነው።
ይኸው ድንበር በዔቅሮን ሰሜናዊ ኮረብታ ከፍ በማለት ወደ ሺከሮን አቅጣጫ ይታጠፍና የባዓላን ኮረብታና እንዲሁም ያብኒኤልን አልፎ ይሄዳል፤ መጨረሻውም የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤
ስለዚህም የቃል ኪዳኑ ታቦት ዔቅሮን ተብላ ወደምትጠራው ወደ ሌላይቱ የፍልስጥኤማውያን ከተማ እንዲወሰድ አደረጉ፤ ነገር ግን እዚያ በደረሰ ጊዜ ኗሪዎቹ እየጮኹ በማልቀስ “የእስራኤልን አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ወደዚህ ያመጡብን እኛን ሁላችንን ለመፍጀት አስበው ነው!” አሉ።
ስለ በደላቸው የሚከፈሉ ስጦታዎች ይሆኑ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ለእግዚአብሔር የላኩአቸው በእባጮች አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች አሽዶድ፥ ጋዛ፥ አስቀሎና፥ ጋትና ዔቅሮን ተብለው በሚጠሩት ከተሞቻቸው ስም የተላኩ ነበሩ፤