ኢያሱ 13:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሮቤልና የጋድ ነገዶች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በርስትነት የሰጣቸውን ምድር ቀደም ብለው ተረክበዋል። ይህም ምድር የሚገኘው በስተምሥራቅ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌላው የምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ የሮቤል ነገድና የጋድ ነገድ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ እንደየድርሻቸው ከፋፍሎ በመደበላቸው መሠረት፣ ራሱ ሙሴ የሰጣቸውን ርስት ተቀበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ባርያ ሙሴ እንደሰጣቸው ከሌሎቹ የምናሴ ነገድ እኩሌታ ጋር የሮቤልና የጋድ ልጆች በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀበሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደ ሰጣቸው ከእርሱ ከምናሴ ጋር የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንደ ሰጣቸው ከእርሱ ከምናሴ ጋር የሮቤልና የጋድ ልጆች በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀበሉ። |
እስራኤላውያን ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ አራባ ሁሉ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ በኩል አሸንፈው ምድራቸውን የያዙባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤
እንግዲህ እነዚህ ሁለት ነገሥታት በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴና በእስራኤል ሕዝብ ጦርነት ድል ሆነው ነበር፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም ይህን ምድር ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው።
ግዛታቸውም ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከሆነው ከዓሮዔር ተነሥቶ እንዲሁም በሸለቆው መካከል ካለው ከተማ ከሜዴባ ሜዳ እስከ ዲቦን ድረስ ይደርሳል።
እነሆ አሁን አምላካችሁ እግዚአብሔር በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለወገኖቻችሁ ለእስራኤላውያን ሰላምን ሰጥቶአቸዋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ወደ ሰጣችሁ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ወደሚገኘውና ርስት አድርጋችሁ ወደ ወረሳችሁት ምድር ተመልሳችሁ ሂዱ፤
ከዕብራውያን መካከል አንዳንዶቹ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ጋድና ወደ ገለዓድ ግዛቶች ሄዱ። ሳኦል ግን እስከዚህ ጊዜ ድረስ በጌልገላ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበረው ሠራዊት ከፍርሃት የተነሣ ይንቀጠቀጥ ነበር፤