Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “በዚያን ጊዜ ከእነዚህ ከሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት በዮርዳኖስ ምሥራቅ፥ ከአርኖን ወንዝ እስከ ሔርሞን ተራራ ያለውን ምድር ሁሉ ያዝን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ በዚያ ጊዜ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ የሚገኘውን፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ ያለውን ግዛት፣ ከእነዚህ ከሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት ላይ ወሰድንባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በዚያን ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩት ሁለቱ አሞራውያን ነገሥታት እጅ፥ ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ ሔርሞን ተራራ ድረስ፥ ምድሪቱን ወሰድን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “በዚ​ያም ዘመን ከአ​ር​ኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ ኤር​ሞን ድረስ ምድ​ሪ​ቱን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ከነ​በሩ ከሁ​ለቱ ከአ​ሞ​ሬ​ዎን ነገ​ሥ​ታት እጅ ወሰ​ድን፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በዚያም ዘመን ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ ምድሪቱን በዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩ ከሁለቱ ከአሞራውያን ነገሥታት እጅ ወሰድን፤

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 3:8
12 Referencias Cruzadas  

ጌቤር የተባለው የኡሪ ልጅ፦ በአሞራውያን ንጉሥ ሲሖንና በባሳን ንጉሥ ዖግ ትገዛ የነበረችው የገለዓድ ግዛት አስተዳዳሪ። እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን አስተዳዳሪዎች የሚቈጣጠር በመላ አገሪቱ ሌላ አንድ የበላይ ኀላፊ ነበር።


በስተ ምሥራቅ ያለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ በስተ ሰሜን እስከ ባዓልሔርሞን፤ እስከ ሠኒርና እስከ ሔርሞን ተራራ በሚደርሰው በባሳን ግዛት ውስጥ ይኖሩ ነበር፤ የሕዝባቸውም ቊጥሩ እየበዛ ሄደ፤


አምላኬ ሆይ! ተስፋ ቈርጬአለሁ ስለዚህም ከዮርዳኖስና ከሔርሞን ምድር ከሚዛር ተራራ አስብሃለሁ።


በፏፏቴህ ድምፅ ጥልቁ ጥልቁን ይጠራል፤ ማዕበልህና ሞገድህ በእኔ ላይ አለፈ።


አንተ ሰሜንና ደቡብን ፈጠርክ፤ የታቦርና የሔርሞን ተራራዎች ለአንተ በደስታ ይዘምራሉ።


በዚያን ጊዜ እነርሱ የእርሱን ምድርና እንዲሁም በዮርዳኖስ ምሥራቅ የምትገኘውን ባሳንን ይገዛ የነበረውን የሌላውን አሞራዊ ንጉሥ የዖግን ምድር ወረሱ።


ይህም ምድር ከዓሮዔር ከተማ በመነሣት በአርኖን ወንዝ ጫፍ አልፎ በሰሜን በኩል እስከ ሢርዮን ተራራ የሚደርስ ነው፤ ይህም የሢርዮን ተራራ ተብሎ የሚጠራው የሔርሞን ተራራ ነው።


እስራኤላውያን ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ አራባ ሁሉ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ በኩል አሸንፈው ምድራቸውን የያዙባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤


የሮቤልና የጋድ ነገዶች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በርስትነት የሰጣቸውን ምድር ቀደም ብለው ተረክበዋል። ይህም ምድር የሚገኘው በስተምሥራቅ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos