ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው።
ዮሐንስ 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁንም ከአንቺ ጋር ያለው ሰው ባልሽ አይደለም፤ ስለዚህ እውነቱን ተናግረሻል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ ዐምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁን ከአንቺ ጋራ ያለውም ባልሽ ስላልሆነ፣ የተናገርሽው እውነት ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምስት ባሎች ነበሩሽና፤ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነቱን ተናገርሽ፤” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀድሞ አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ ዛሬ አብሮሽ ያለው ግን ባልሽ አይደለም፤ ይህንስ እውነት አልሽ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ አላት። |
ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው።
“አንድ ሰው ሚስቱ በእርሱ ላይ እንዳመነዘረችበት ቢጠረጥርና ቅናት ቢያድርበት የሚፈጽመው የሕግ ሥርዓት የሚከተለው ነው፦ ይኸውም ሴትዮዋን በመሠዊያው ፊት ለፊት እንድትቆም ያደርግና ካህኑ ከላይ የተጠቀሰውን ሥርዓት ይፈጽምባታል፤ ወይም የቅናት መንፈስ በአንድ ሰው ላይ ቢያድርና ሚስቱን ቢጠራጠር ወደ መሠዊያው ፊት አምጥቶአት ካህኑ ይህን የሕግ ሥርዓት ይፈጽምባት፤
ስለዚህ ባልዋ በሕይወት እያለ ሌላ ወንድ ብታገባ አመንዝራ ትባላለች። ባልዋ ከሞተ ግን ከእርሱ ጋር ከታሰረችበት ሕግ ነጻ ትወጣለች፤ ሌላ ወንድ ብታገባም አመንዝራ አይደለችም።
ጋብቻ በሁሉ ዘንድ የተከበረ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን እግዚአብሔር ስለሚፈርድባቸው ባልና ሚስት ታማኝነትን በማጒደል ጋብቻን አያርክሱ።
በተጨማሪም የሟቹ የማሕሎን ሚስት ሞአባዊቷ ሩት ሚስቴ ትሆናለች፤ ይህም ንብረቱ ከሟቹ ቤተሰብ እንዳይወጣና የትውልድ ሐረጉም ከወንድሞቹ መካከልና ከሀገሩ አደባባይ እንዳይጠፉ ያደርገዋል፤ ለዚህ ሁሉ ዛሬ እናንተ ምስክሮች ናችሁ።”