እነሆ፥ እኔ የሽብር ወሬ የሚያሰማ መንፈስ እልክበታለሁ፤ ስለዚህም ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲሄድና እዚያም በገዛ ምድሩ በሰይፍ ተመትቶ እንዲሞት አደርጋለሁ።’ ”
ኤርምያስ 49:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከሁሉም አቅጣጫ ሽብር አመጣባችኋለሁ፤ ሁላችሁም ትሸሻላችሁ፤ ሁሉም ወደፊቱ ሸሽቶ ስለሚበታተን የሸሹትን ስደተኞች የሚሰበስብ አይገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ፣ ሽብር አመጣብሻለሁ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “እያንዳንዳችሁ ትሰደዳላችሁ፤ በሽሽት ላይ ያሉትንም የሚሰበስብ አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ በአንቺ ላይ ፍርሃትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፥ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ ፍርሀትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፤ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ ፍርሃትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፥ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም። |
እነሆ፥ እኔ የሽብር ወሬ የሚያሰማ መንፈስ እልክበታለሁ፤ ስለዚህም ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲሄድና እዚያም በገዛ ምድሩ በሰይፍ ተመትቶ እንዲሞት አደርጋለሁ።’ ”
የሞአብ መልእክተኞች ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ምን ማድረግ እንደሚገባን ምከሩን፤ በቀትር ጊዜ የእናንተ ጥላ እንደ ሌሊት ጨለማ ይከልለን።
በምድራችሁ ላይ የሚገኙት ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ብዛታቸው ከባሕር አሸዋ የሚበልጥ ሆኖአል፤ በእኩለ ቀን በወጣቶች እናቶች ላይ ሞትን አመጣለሁ በእነርሱም ላይ ሽብርንና ጭንቀትን በቅጽበት አመጣለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን ሕዝብ እንደ ዓሣ የሚያጠምዱና እንደ አውሬ የሚያድኑ ብዙ ሰዎችን እልካለሁ፤ በየተራራውና በየኰረብታው በቋጥኞች ውስጥ ባሉ ዋሻዎችም እያደኑ ይይዙአቸዋል።
እግዚአብሔር ራሱ እንዲህ ብሎአል፦ ‘ለራስህና ለጓደኞችህም ጭምር አሸባሪ ላደርግህ ነው፤ እነርሱም ሁሉ በጠላቶቻቸው ሰይፍ ሲገደሉ ታያለህ፤ የይሁዳን ሕዝብ ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ ሥልጣን ሥር አደርጋለሁ፤ እርሱ እኩሌቶቹን እስረኛ አድርጎ ወደ ባቢሎን ይወስዳቸዋል፤ እኩሌቶቹንም እዚሁ ይገድላቸዋል።
“ነገር ግን ይህ የማየው ነገር ምንድን ነው? ከፍርሃት የተነሣ ወደ ኋላ በመመለስ ላይ ናቸው፤ ወታደሮቻቸው ድል ሆኑ፤ በየአቅጣጫው ፍርሀትና ሽብር ስላለ ወደ ኋላ መለስ ብለው ሳያዩም ወደ ፊት ሸሹ።
ድንኳኖቻቸውን፥ መንጋዎቻቸውን፥ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ሁሉ ውሰዱ፤ ግመሎቻቸውን ለራሳችሁ ውሰዱ። ‘በዙሪያው ሽብር ተነሥቷል’ ብለው ይጮኻሉ።”
ስለዚህም ሕዝቡ “ወዲያ ሂዱ! ስለ ረከሳችሁም አትንኩን!” እያሉ ይጮኹባቸዋል። ስለዚህ እነርሱ ስደተኞችና ተንከራታቾች ሆኑ ሕዝቦችም “ከእንግዲህ በመካከላችን አይቈዩም” አሉ።
እንዲህ አለቻቸው፦ “የሀገሪቱ ኗሪዎች በሙሉ በፍርሃት ተውጠው ልባቸው ቀለጠ፤ በሁላችንም ላይ ፍርሀት ስላደረብን እግዚአብሔር ምድሪቱን ለእናንተ እንደ ሰጠ ዐውቃለሁ፤