ኤርምያስ 48:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞአብ መከላከያ ኀይል ተሰብሮአል፤ ሥልጣንዋም ተገፎአል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞዓብ ቀንድ ተቈርጧል፤ እጁም ተሰባብሯል፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞዓብ ቀንድ ተቈረጠ ክንዱም ተሰበረ፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞአብ ቀንድ ተሰበረ፤ እጁም ተቀጠቀጠ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሞዓብ ቀንድ ተቈረጠ ክንዱም ተሰበረ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
በኀይለኛ ቊጣው የእስራኤልን ኀይል ሁሉ አዳከመ፤ ጠላትም እያየ ለእነርሱ የሚሰጠውን ድጋፍ አቋርጦ፥ በያዕቆብም ዘር ላይ እንደሚንበለበል እሳት ቊጣውን አቀጣጠለ፤ ቊጣው ጐረቤቶቹንም ሁሉ አወደመ።
እኔም ስለ ቀንዶቹ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ ከቀንዶቹ መካከል ሌላ አንድ ትንሽ ቀንድ ወጣ፤ ለእርሱም ቦታ ለመልቀቅ ከፊተኞቹ ቀንዶች ሦስቱ ተነቀሉ፤ ይህም ትንሽ ቀንድ የሰው ዐይኖችና በትዕቢት የሚናገር አንደበት ነበረው።