Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘካርያስ 2:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በሌላም ራእይ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰው አየሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ደግሞም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰውም በፊቴ አየሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዐይኖቼንም አንሥቼ እነሆም አራት ቀንዶች አየሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዓይኖቼንም አነሣሁ፣ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዓይኖቼንም አነሣሁ፥ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 2:1
12 Referencias Cruzadas  

“እነሆ፥ በወናፉ ፍሙን የሚያናፋውን ብረት አቅላጭ የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ እርሱም መሣሪያውን የሚሠራው ለየተሠራለት ዓላማ እንዲውል ለማድረግ ነው፤ ያጠፋ ዘንድ አጥፊውን የፈጠርኩ እኔ ነኝ።


የወሰኑም መስመር ከማእዘኑ ቅጥር በር ወደ ጋሬብ ኰረብታ ይሄድና ወደ ጎዓ ይዞራል።


የሞአብ መከላከያ ኀይል ተሰብሮአል፤ ሥልጣንዋም ተገፎአል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ወደዚያ ሲወስደኝም እንደ ነሐስ የሚያበራ መልክ ያለውን አንድ ሰው አየሁ፤ እርሱም ከበፍታ የተሠራ ገመድና መለኪያ ዘንግ ይዞ በቅጽሩ በር አጠገብ ቆሞ ነበር።


በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ቅጥር ነበረ፤ በሰውዬው እጅ ያለው መለኪያ ዘንግ በእርሱ ረጃጅም ክንዶች ስድስት ይሆናል፤ የቅጽሩ ስፋት ሲለካ አንድ ዘንግ፥ ከፍታው ሲለካ አንድ ዘንግ ሆነ። የእርሱ ክንድ ግን በሌሎች ሰዎች ክንድ ሲለካ አንድ ክንድ ከጋት ይሆናል።


ያም ሰው በያዘው የመለኪያ ገመድ ወደ ምሥራቅ የሚፈሰውን ውሃ በመከተል አንድ ሺህ ክንድ ለካ፤ በዚያም ውሃ እየተራመድኩ እንድሻገር አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ቊርጭምጭሚቴ ደረሰ።


እንደገናም አንድ ሺህ ክንድ ለካና እንድራመድ አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ጒልበቴ ደረሰ፤ ቀጥሎም አንድ ሺህ ክንድ ለክቶ በውሃው ውስጥ እንድራመድ አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ወገቤ ደረሰ።


“ከዚያ በኋላ አራተኛውን አውሬ አየሁ፤ እርሱም አስፈሪ፥ አስደንጋጭና በጣም ኀይለኛ ነበር፤ ይህም አውሬ የሚቦጫጭቅባቸውና የሚሰባብርባቸው ታላላቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት። የተረፈውንም በእግሮቹ ይረግጠው ነበር፤ ካለፉትም አውሬዎች ሁሉ የተለየ ሆኖ ዐሥር ቀንዶች ነበሩት።


ስለዚህ ለከተማይቱ ምሕረትን ለማሳየት ወደ ኢየሩሳሌም እመለሳለሁ ቤተ መቅደሴና ከተማይቱ እንደገና ታድሰው ይሠራሉ።”


በሌላም ራእይ አራት የበሬ ቀንዶችን አየሁ፤


ከዚህ በኋላ ለመለኪያ እንደሚያገለግል በትር ያለ አንድ ሸንበቆ ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባልኩ፦ “ተነሥ፤ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና መሠዊያውን ለካ፤ በዚያ የሚያመልኩትንም ቊጠር፤


የተናገረኝም መልአክ ከተማይቱንና ደጃፎችዋን፥ የግንቡንም አጥር የሚለካበት የወርቅ ዘንግ ነበረው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos