ኤርምያስ 4:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለምለሚቱ ምድር ወደ በረሓነት ተለውጣለች፤ ከእግዚአብሔር ብርቱ ቊጣ የተነሣ፥ ከተሞችዋ ሁሉ ፈራርሰዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተመለከትሁ፤ እነሆም፣ ፍሬያማው ምድር በረሓ ሆነ፤ ከተሞቹ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት፣ ከብርቱ ቍጣው የተነሣ ፈራረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማው እርሻ ምድረ በዳ ሆኖ፥ ከተሞችም ሁሉ ከጌታ ፊት ከጽኑ ቁጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተመለከትሁ፤ እነሆም ቀርሜሎስ ምድረ በዳ ሆነች፤ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ በእሳት ተቃጠሉ፤ ከጽኑ ቍጣውም የተነሣ ፈጽመው ጠፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፥ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር። |
“እኛ የምናደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አያይም” ከሚሉት ሕዝባችን ክፋት የተነሣ፥ ምድራችንን ድርቅ የሚያጠቃውና በየመስኩ ያለውስ ሣር እንደ ደረቀ የሚቀረው እስከ መቼ ነው? በዚህም ምክንያት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ተጠራርገው ጠፍተዋል።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሁሉም ወና ስለ ሆኑና በእነርሱም ላይ የሚዘዋወርባቸው ስለሌለ፥ ስለ ተራራዎች አዝናለሁ፤ ስለ ሜዳዎችም አለቅሳለሁ፤ የከብቶች ድምፅ ዳግመኛ አይሰማም፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ሁሉ ሸሽተው ጠፍተዋል።”
እግዚአብሔር መሠዊያውን ናቀ፤ መቅደሱንም ተወ፤ የቤተ መንግሥቶችዋን ቅጽሮች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ፤ በበዓላት ቀን እንደሚደረገው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከፍተኛ ድምፅ ተሰማ።
ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ ቤተ መቅደሱም የተሠራበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ይሆናል።
እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው።