Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 107:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 እዚያ ከሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን አገር እንደ ጨው ምድር የማታፈራ አደረጋት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ ፍሬያማዋን ምድር በጨው የተበከለች አደረጋት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን ምድር ጨው አደረጋት።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 107:34
12 Referencias Cruzadas  

ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።


በዚያን ዘመን የሰዶም ሰዎች እጅግ ክፉዎችና እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑ ኃጢአተኞች ነበሩ።


እነዚህ ነገሥታት አንድ ግንባር ፈጥረው አሁን ሙት ባሕር ተብሎ በሚጠራው በሲዲም ሸለቆ ጦርነት ገጠሙ፤


ምድርንም በምታርስበት ጊዜ ምንም ፍሬ አትሰጥህም፤ በምድር ላይም ስደተኛ ሆነህ ትንከራተታለህ።”


አምላክ ሆይ! ሕዝብህን በመራህ ጊዜ፥ በበረሓም አብረሃቸው በተጓዝህ ጊዜ፥


“እኛ የምናደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አያይም” ከሚሉት ሕዝባችን ክፋት የተነሣ፥ ምድራችንን ድርቅ የሚያጠቃውና በየመስኩ ያለውስ ሣር እንደ ደረቀ የሚቀረው እስከ መቼ ነው? በዚህም ምክንያት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ተጠራርገው ጠፍተዋል።


በደላችሁ በረከትን አሳጣችሁ፤ የኃጢአታችሁም ብዛት መልካም ነገር እንዳታገኙ አደረገ።


በምድሪቱ ለሚኖሩ ሕዝብ ጌታ እግዚአብሔር በእስራኤል ምድር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሕዝብ እንዲህ ይላል ብለህ ንገራቸው፦ ‘በምድሪቱ በሚኖሩ ሰዎች ዐመፅ ምክንያት ምድሪቱ በጠቅላላ ስለምትራቈት ምግባቸውን የሚበሉት በፍርሃት ነው፤ ውሃቸውንም የሚጠጡት ተስፋ በመቊረጥ ነው።


ነገር ግን ረግረጉና እቋሪው ውሃ የጨው መከማቻ እንደ ሆነ ይቀራል እንጂ የጠራ ውሃ አይሆንም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos