ኢሳይያስ 5:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እንደ ባሕር ማዕበል እየተመሙ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ይመጡባቸዋል፤ እነሆ ወደ ምድር ቢመለከቱ በጨለማና በመከራ እንደ ተከበቡ ያያሉ፤ ከደመናውም የተነሣ ብርሃኑ ይጨልማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኹበታል፤ ማንም ወደ ምድር ቢመለከት፣ ጨለማንና መከራን ያያል፤ ብርሃን እንኳ በደመናዎች ይጋረዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኹበታል፤ ማንም ወደ ምድር ቢመለከት፥ ጨለማንና መከራን ያያል፤ ብርሃን እንኳ በደመናዎች ይጋረዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እንደ ባሕር መትመም ይተምሙባቸዋል፤ ወደ ምድርም ይመለከታሉ፤ ድቅድቅ ጨለማን ያያሉ፤ ይጨነቃሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን እንደ ባሕር መትመም ይተምሙባቸዋል፥ ወደ ምድርም ቢመለከቱ፥ እነሆ፥ ጨለማና መከራ አለ፥ ብርሃንም በደመናዎችዋ ውስጥ ጨልሞአል። |
በተራሮች ላይ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ፤ ይህም ጩኸት በአንድነት የተሰበሰቡ የብዙ ሕዝብ መንግሥታት ሁካታ ነው፤ የሠራዊት አምላክ ሠራዊቱን ለጦርነት እያዘጋጀ ነው፤
በደቡባዊ በረሓ ስለሚኖሩ እንስሶች የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ “መልእክተኞቹ የአንበሶች መኖሪያ፥ የመርዘኛ እባቦችና የበራሪ ዘንዶዎች መስለክለኪያ በሆነ አደገኛ አገር አቋርጠው ይሄዳሉ፤ በአህዮቻቸውና በግመሎቻቸው ውድ የሆኑ ስጦታዎችን ጭነው ምንም ርዳታ ልትሰጣቸው ወደማትችል አገር ይሄዳሉ።
ሕዝቡ እንዲህ ይላሉ፦ “ፍትሕ ከእኛ ርቆአል፤ ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም፤ ብርሃን እንዲበራልን እንፈልጋለን፤ ነገር ግን ሁሉም ጨለማ ነው፤ ስለዚህ በድቅድቅ ጨለማ እንመላለሳለን።
ጨለማን አምጥቶ በተራራዎች ከመሰናከላችሁ በፊት ተስፋ ያደረጋችኹትን ብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ወደ ጥልቅ ጭጋግ ከመለወጡ በፊት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ።
ቀስታቸውንና ሰይፋቸውን ይዘዋል፤ እነርሱ ምሕረት የሌላቸው ጨካኞች ናቸው፤ ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፥ ድምፃቸው እንደሚተም ባሕር ነው፤ ባቢሎን ሆይ! እነርሱ በአንቺ ላይ አደጋ ለመጣል ለዘመቻ ተዘጋጅተው እንደሚመጡ ሰዎች ወደ አንቺ እየመጡ ነው።
ቀስታቸውንና ሰይፋቸውን አንሥተዋል፤ እነርሱም ምሕረት የሌላቸው ጨካኞች ናቸው፤ ተቀምጠው የሚጋልቡአቸው ፈረሶች፥ የኮቴአቸው ድምፅ እንደ ባሕር ሞገድ ነው። እነሆ እነርሱ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት ተዘጋጅተዋል።”
“ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ጢሮስ ሆይ! እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቼ ባሕር ሞገድን እንደሚያስነሣ በአንቺ ላይ ብዙ ሕዝቦቼን አስነሣለሁ።
እናንተ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት የምትጠባበቁ ወዮላችሁ! ያ ቀን የጨለማ እንጂ የብርሃን ቀን ስላይደለ ለምን ያንን ቀን ትጠባበቃላችሁ?
“ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ።
ከዚህ በኋላ በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለከትኩ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይ እንደ ጥቊር የሐዘን ልብስ ጠቈረች፤ ጨረቃም በሙሉ እንደ ደም ቀላች፤