ኢሳይያስ 43:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰምጡህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ወንዞችም አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፥ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም። |
በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።
እግዚአብሔርም መልሶ “አይዞህ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔ እንደ ላክኹህም ምልክት የሚሆንህ ይህ ነው፤ ሕዝቤን ከግብጽ በምታወጣበት ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እኔን ታመልኩኛላችሁ” አለው።
የሠራዊት ጌታ አምላክ ነጐድጓድን፥ የመሬት መናወጥን፥ ታላቅ ድምፅን፥ ዐውሎ ነፋስን፥ ሞገድንና የሚባላ የእሳት ነበልባልን በጠላቶችሽ ላይ በመላክ አንቺን ይታደግሻል።
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ኀይልና ግርማ ከሩቅ ይታያል፤ ነበልባልና ጢስ የቊጣው ምልክቶች ናቸው፤ በሚናገርበትም ጊዜ ቃሉ እንደ እሳት ይነዳል።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
እኔ ከእናንተ ጋራ ስለ ሆንኩ አገልጋዮቼ እስራኤላውያን ሆይ! እናንተ አትፍሩ፤ እናንተ በሀገራቸው እንድትበታተኑ ያደረግኹባቸውን ሕዝቦች ሁሉ አጠፋለሁ፤ እናንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋችሁም፤ ሆኖም ለማረም እቀጣችኋለሁ፤ ሳልቀጣችሁ ግን አላልፍም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
የእግዚአብሔር መልእክተኛ የሆነው ሐጌ ለሕዝቡ “ ‘እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ይላል እግዚአብሔር” ሲል የእግዚአብሔርን መልእክት አስተላለፈ።
እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።
እስራኤላውያን በደረቅ ምድር እንደሚሻገሩ ሆነው ቀይ ባሕርን የተሻገሩት በእምነት ነው፤ ግብጻውያን ግን እንዲሁ ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ሁሉም ሰጠሙ።
አንተ ኢያሱ፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ አንተን ተቋቊሞ ድል የሚነሣህ ማንም አይኖርም፤ እኔ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ፤ ከቶም አልተውህም፤