ዘፍጥረት 43:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤቱም አዛዥ “በዚህ ጉዳይ ጭንቀትና ፍርሀት አይድረስባችሁ፤ የእናንተና የአባታችሁ አምላክ ይህን ገንዘብ በየስልቻዎቻችሁ አስቀምጦላችሁ ይሆናል፤ የእናንተን ገንዘብ ግን እኔ ተቀብዬአለሁ” አላቸው። ከዚህ በኋላ ስምዖንን ወደ እነርሱ አመጣው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤቱ አዛዥም፣ “አይዟችሁ አትፍሩ፤ በየስልቾቻችሁ ውስጥ ያገኛችሁትን ገንዘብ የሰጣችሁ የእናንተም የአባቶቻችሁም አምላክ ነው፤ እኔ እንደ ሆንሁ ብሩን ተቀብያለሁ” አላቸው። ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ አገናኛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤቱ አዛዥም፥ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ በየስልቾቻችሁ ውስጥ ያገኛችሁትን ገንዘብ የሰጣችሁ የእናንተም የአባቶቻችሁም አምላክ ነው፤ እኔ እንደሆንኩ ብሩን ተቀብያለሁ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አላቸው፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ አምላካችሁ የአባቶቻችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁንስ መዝኜ ተቀብያለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አላቸው፦ ስላም ለእናንተ ይሁን አትፍሩ አምላካችሁና የአባታችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ ብራችሁስ ደርሶኛል። |
እርሱም ለወንድሞቹ “ገንዘቤ ተመልሶልኛል፤ ይኸው በስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት!” ብሎ ነገራቸው። ሁሉም በፍርሃት ተንቀጥቅጠው “እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ።
በዚህ ጊዜ አባታቸው “ልጆቼን ሁሉ እንዳጣ ትፈልጋላችሁን? ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ለመውሰድ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ!” አለ።
ብንያምንና ሌላውንም ወንድማችሁን መልሶ እንዲሰጣችሁ ሁሉን የሚችል አምላክ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እኔ በበኩሌ ልጆቼን ካጣሁ፥ ባዶ እጄን መቅረቴ ነው።”
የእግዚአብሔር መንፈስ የሠላሳዎቹ መሪ በሆነው በዐማሳይ ላይ ወረደ፤ እርሱም፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን! የእሴይ ልጅ ዳዊት ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን! ለአንተና አንተን ለሚረዱ ሁሉ ሰላም ይሁን! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር በመሆን ይረዳሃል፤” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ዳዊትም እነርሱን በደስታ ተቀብሎ በሠራዊቱ ውስጥ አለቆች አደረጋቸው።
ዳዊት፥ ንጉሥ ሳኦልን ለመውጋት ከፍልስጥኤማውያን ጋር በዘመተ ጊዜ ከምናሴ ነገድ የሆኑ ጥቂት ወታደሮች ከዳዊት ጋር ለመተባበር ሄዱ፤ ሆኖም የፍልስጥኤማውያን መሪዎች “ዳዊት እኛን ከድቶ ወደ ቀድሞ ጌታው ወደ ሳኦል ይመለሳል” ብለው ስለ ፈሩ ከተመካከሩ በኋላ ወደ ቲግላግ እንዲመለስ አደረጉት፤
ንጉሠ ነገሥቱም ለዚህ ደብዳቤ ከዚህ የሚከተለውን መልስ ላከ፦ “ለአገረ ገዢው ረሑም፥ ለአውራጃ ጸሐፊው ሺምሻይ፥ እንዲሁም በሰማርያና ከኤፍራጥስ በስተ ምዕራብ ለሚኖሩ ተባባሪዎችህ ሁሉ፥ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
“ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዐይነት አይደለም፤ ልባችሁ አይጨነቅ፤ ደግሞም አይፍራ።
በዚያው በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን እሑድ ማታ ደቀ መዛሙርቱ የአይሁድን ባለሥልጣኖች በመፍራት፥ በራፎቹን ዘግተው፥ በቤት ውስጥ ተሰብስበው ነበር፤ በሮቹ ተዘግተው ሳለ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ተሰበሰቡበት ቤት ገባ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው።
ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ እንደገና በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም አብሮአቸው ነበር፤ በሮቹ ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጥቶ በመካከላቸው ቆመና “ሰላም ለእናንተ ይሁን!” አላቸው።
ለናባልም ይነግሩት ዘንድ እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጣቸው፦ “ሰላም ላንተ፥ ሰላም ለቤትህ፥ ሰላም ያንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን ብላችሁ ሰላምታ አቅርቡለት።