ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።”
ዘዳግም 6:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያች ምድር ለረጅም ዘመናት መኖር እንድትችሉ አንተና ልጆችህ፥ የልጅ ልጆችህም በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን መፍራትና እኔ ለሰጠኋችሁ ደንቦችና ትእዛዞች ታዛዦች መሆን ይገባችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም፣ የምሰጣችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፣ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም፣ አንተ፣ ልጆችህና ከእነርሱ በኋላ የሚመጡት ልጆቻቸው በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትፈሩት ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፤ ጌታ አምላክህን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን፥ ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ፥ ልጆቻችሁም፥ የልጅ ልጆቻችሁም በዕድሜአችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፈርታችሁ እኔ ለእናንተ ያዘዝሁትን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ፥ ዕድሜአችሁም ይረዝም ዘንድ፤ |
ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።”
መልአኩም “ልጁን አትንካ፤ ምንም ዐይነት ጒዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት ስለ አልተቈጠብክ እነሆ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቼአለሁ።”
በዚህም ዐይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ።
እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙን የሚፈጽሙትን ሁሉ አስተዋዮች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
ሙሴም “አይዞአችሁ፥ አትፍሩ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሁኔታ ወደ እናንተ የመጣው ሊፈትናችሁና እርሱን በመፍራት ኃጢአት ከመሥራት ርቃችሁ እንድትኖሩ ነው” ሲል መለሰላቸው።
ነገር ግን ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ እነግራችኋለሁ፤ ይኸውም ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን እግዚአብሔርን ነው፤ አዎ፥ እርሱን ብቻ ፍሩ እላችኋለሁ!
ትእዛዞቹንም ብትጠብቁ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለዘሮቻቸው ሊሰጣቸው ቃል በገባላቸው በማርና በወተት በበለጸገችው፥ በዚያች ለምለም ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራላችሁ።
አምላካችሁን እግዚአብሔርን ተከተሉት፤ እርሱን ብቻ ፍሩ፤ ትእዛዞቹንም ጠብቁ፤ ቃሉንም ስሙ፤ እርሱንም አምልኩ፤ ከእርሱም ጋር ያላችሁ አንድነት የጠበቀ ይሁን።
እነሆ፥ እኔ በሕይወትና በሞት መካከል፥ በእግዚአብሔር በረከትና መርገም መካከል ምርጫ እሰጣችኋለሁ፤ በምታደርጉትም ምርጫ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ ምስክር አድርጌ እጠራለሁ፤ ስለዚህም እናንተና ዘሮቻችሁ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጡ።
አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፤ ለእርሱም ታዛዥ ሁን፤ በእርሱም እመን፤ ይህም ለአንተ ሕይወት ከመሆኑም በላይ ለቀድሞ አባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል በገባላቸው መሠረት ገብተህ በምትኖርባት ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራለህ።”
እግዚአብሔር ‘ቃሌን ይሰሙ ዘንድ ስለምፈልግ ሕዝቡን ሰብስብ’ ባለኝ ጊዜ በሲና ተራራ ላይ በእግዚአብሔር ፊት በቆማችሁበት ቀን ‘በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለእኔ እንዲታዘዙና፥ ልጆቻቸውም እኔን መፍራትን ያውቁ ዘንድ ያስተምሩአቸው’ ያለውን አስታውሱ።
እግዚአብሔር አምላካችሁ ለዘለዓለም እንድትኖሩባት በሚያወርሳችሁ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖሩ ዘንድ ለእናንተና ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላቸው እኔ ዛሬ የማዛችሁን ሕጉንና ትእዛዞቹን ጠብቁ።”
እንግዲህ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን በዐይናችሁ ያያችሁትን ሁሉ እንዳትረሱና ከአእምሮአችሁ እንዳይጠፋ ተጠንቀቁ። ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤
“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ባዘዝኩህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።
“አሁን ተሻግራችሁ በርስትነት በሚሰጣችሁ ምድር እንድትጠብቁት እግዚአብሔር አምላክህ እንዳስተምርህ ያዘዘኝ ትእዛዞች፥ ሕግና ሥርዓት እነዚህ ናቸው።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር አምላካችን እነዚህን ደንቦች እንድንፈጽምና እርሱንም እንድንፈራው አዞናል፤ እኛም ይህን ብናደርግ እርሱ ዘወትር ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ እንዲከናወንልን ያደርጋል፤ ዛሬ እንደሚያደርገውም ሁሉ በሕይወት ያኖረናል፤
እነዚህኑ ትእዛዞች ለልጆችህ አስተምራቸው፤ በቤት ስትቀመጥም ሆነ በመንገድ ስትሄድ፥ ዕረፍት በምታደርግበትም ጊዜ ሆነ ሥራ በምትሠራበት ጊዜ ሁሉ፥ እነዚህን ትእዛዞች ዘወትር አሰላስል፤
በዚህም ምክንያት በምድር ላይ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ እንደ ሆነ ይገነዘባል፤ እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔርን ለዘለዓለም ታከብራላችሁ።”
ለማንም ሳያዳላ ለያንዳንዱ እንደየሥራው የሚፈርደውን እግዚአብሔርን “አባታችን” ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ በዚህ ዓለም በእንግድነት መጻተኞች ሆናችሁ ስትኖሩ እርሱን በመፍራት ኑሩ።