ዳንኤል 2:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራ ላይ ተፈንቅሎ በመውረድ ከብረት፥ ከነሐስ፥ ከሸክላ፥ ከብርና ከወርቅ የተሠራውን ምስል ያደቀቀውም ድንጋይ፥ ያ መንግሥት ነው፤ በዚህም ታላቁ አምላክ ወደፊት የሚሆነውን ሁሉ አሳይቶሃል፤ እነሆ፥ ሕልሙ እውነት ነው፤ አስተማማኝ ትርጒሙም ይኸው ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ የወረደውና ብረቱን፣ ናሱን፣ ሸክላውን፣ ብሩንና ወርቁን ያደቀቀው ድንጋይ ራእይ ትርጓሜ ይህ ነው፤ “ታላቁ አምላክ ወደ ፊት የሚሆነውን ለንጉሡ አሳይቶታል፤ ሕልሙ እውነት ነው፤ ትርጓሜውም የታመነ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋዩም እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ ብረቱንና ናሱን ሸክላውንና ብሩን ወርቁንም ሲፈጨው እንዳየህ፥ እንዲሁ ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ታላቁ አምላክ ለንጉሡ አስታውቆታል፥ ሕልሙም እውነተኛ ፍቺውም የታመነ ነው። |
ሕዝቡ ተጨንቀው ስላየሁ፥ እነርሱንና መሪዎቻቸውን፥ ሌሎችንም ባለሥልጣኖች ሁሉ “ከጠላቶቻችን የተነሣ አትፍሩ፤ ምን ያኽል ታላቅና ግርማው የሚያስፈራ አምላክ እንዳለንና እርሱ ስለ ወገኖቻችሁ፥ ስለ ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ ስለ ቤት ንብረታችሁም እንደሚዋጋላችሁ አስታውሱ” አልኳቸው።
“ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ፥ ታላቁ፥ ኀያሉና አስፈሪው አምላካችን ሆይ! በእኛ፥ በንጉሦቻችን፥ በመሪዎቻችን፥ በካህኖቻችን፥ በነቢዮቻችን፥ በቅድመ አያቶቻችን፥ እንዲሁም በሕዝብህ ሁሉ ላይ፥ ከአሦር ነገሥታት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ የደረሰውን መከራ ሁሉ አስብ።
ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “እነሆ፥ የጸና የመሠረት ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ እርሱም የተመሰከረለት፥ የከበረ የማእዘን ድንጋይ ነው፤ በእርሱም የሚያምን ሁሉ አይናወጥም።
ከዚህ በኋላ ዳንኤል የባቢሎንን ጠቢባን እንዲገድል ከንጉሡ ትእዛዝ ወደተሰጠው ወደ አርዮክ ሄደና “የባቢሎንን ጠቢባን አትግደል፤ ይልቅስ ወደ ንጉሡ አቅርበኝና የሕልሙን ትርጒም ልንገረው” አለው።
ነገር ግን ምሥጢርን ሁሉ የሚገልጥ አንድ አምላክ በሰማይ አለ፤ እርሱ ወደ ፊት የሚሆነውን ነገር ሁሉ ለአንተ ገልጦልሃል፤ በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለ ያየኸው ሕልምና በአእምሮህ የነበረው ራእይ የሚከተለው ነው።
“ንጉሥ ሆይ! አንተ በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለ ወደ ፊት ስለሚሆነው ነገር ታሰላስል ነበር፤ ስለዚህ ምሥጢርን የሚገልጥ አምላክ ወደፊት የሚሆነውን ነገር አስታወቀህ።
በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይፈርስና ግዛቱም በሌላ ሕዝብ የማይደፈር መንግሥትን ይመሠርታል፤ ይህ መንግሥት ሌሎችን መንግሥታት እስከ መጨረሻው ያጠፋቸዋል፤ እርሱ ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤
እጅግም ተንኰለኛ ስለ ሆነ በማታለል ይበለጽጋል፤ ራሱንም ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ብዙ ሰዎችን ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ይገድላል፤ የልዑላንን ልዑል እንኳ ይፈታተናል፤ በመጨረሻም እርሱ ራሱ ይጠፋል፤ የሚጠፋውም በሰው ኀይል አይደለም።
በዚያን ጊዜ፥ የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ ኀይላቸውንም እንዳልነበረ አደርጋለሁ፤ ሠረገላ ነጂዎችን ከነሠረገሎቻቸው እገለብጣለሁ፤ ፈረሶቻቸው ያልቃሉ፤ ፈረሰኞቻቸውም እርስ በርሳቸው ይጋደላሉ፤
በዚያን ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ እንደ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ እርስዋን ለማንሣት የሚሞክር ሁሉ ራሱን ይጐዳል፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እርስዋን ለማጥቃት ተባብረው ይመጣሉ፤
እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፤ ለጥያቄዬ መልስ ከሰጣችሁኝ እኔም ይህን ሁሉ በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ።
ፈሪሳውያን ኢየሱስን፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?” ሲሉ ጠየቁት፤ እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የእግዚአብሔር መንግሥት የምትመጣው ሰዎች ነቅተው በሚጠባበቁት ዐይነት አይደለም፤
እግዚአብሔር አምላካችሁ ከባዕዳን አማልክት ሁሉና ከኀይላትም ሁሉ በላይ ታላቅና ብርቱ ስለ ሆነ በፍርሃት መከበር ይገባዋል። እርሱ በፍርድ አያዳላም፤ ጉቦም አይቀበልም።
ከዚህ በኋላ በፀሐይ ላይ የቆመ አንድ መልአክ አየሁ፤ እርሱ በሰማይ ለሚበርሩ ወፎች እንዲህ ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ “ወደ ታላቁ የእግዚአብሔር ግብዣ ኑ! ተሰብሰቡ!
ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እነሆ በሰማይ የተከፈተ በር ነበር፤ በመጀመሪያ ሰምቼው የነበረው እንደ እምቢልታ ያለው ድምፅ እንዲህ አለ፦ “ና ወደዚህ ውጣ፤ ወደፊት መሆን የሚገባቸውን ነገሮች አሳይሃለሁ፤”