ሐዋርያት ሥራ 13:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ዳዊት በሕይወቱ ዘመን አገልግሎቱን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከፈጸመ በኋላ ሞቶአል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮአል፤ መበስበስም ደርሶበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዳዊት በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ካገለገለ በኋላ አንቀላፍቷል፤ ከአባቶቹም ጋራ ተቀብሮ ሥጋው በስብሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፤ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊት ግን በዘመኑ ለእግዚአብሔር ትእዛዝ አገልግሎአል፤ እንደ አባቶቹ ሞተ፥ ተቀበረም፤ መፍረስ መበስበስንም አይቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን አሳብ ካገለገለ በኋላ አንቀላፋ፥ ከአባቶቹም ጋር ተጨምሮ መበስበስን አየ፤ |
ዘመንህ ተፈጽሞ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣውን ልጅህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ የእርሱንም መንግሥት አጸናለሁ።
ባለፉት ዘመናት ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እንኳ የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ጦርነት የምትመራ አንተ ነበርክ፤ ‘ሕዝቤን እስራኤልን የምትመራና የምታስተዳድር አንተ ነህ’ ብሎ አምላክህ እግዚአብሔር ነግሮሃል።”
ዖዝያ ሞተ፤ በነገሥታትም መካነ መቃብር አጠገብ ባለው ስፍራ ቀበሩት፤ በነገሥታት መካነ መቃብር ያልተቀበረው የቆዳ በሽታ ስለ ነበረበት ነው፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ።
እነዚህ እንደ በጎች እንዲሞቱና እንዲቀበሩ ይደረጋሉ፤ እረኛ በጎችን እንደሚመራ ሞትም እነዚህን ወደ መቃብር ይመራል፤ ትክክለኞች ሰዎች በማለዳ በመቃብራቸው ላይ ይመላለሳሉ፤ ሥጋቸውም በመቃብር ውስጥ ይበሰብሳል፤ የሙታን ዓለምም መኖሪያቸው ይሆናል። ደጋግ ሰዎችም በማለዳ ተነሥተው በእነርሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ።
ሳኦልንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን አነገሠላቸው፤ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲመሰክር፦ ‘እንደ ፍላጎቴ የሚሆንልኝን፤ ፈቃዴንም የሚፈጽመውን፥ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ’ ብሎአል።
“ወንድሞቼ ሆይ! ከቀድሞ አባቶች አንዱ የሆነው ዳዊት እንደ ሞተና እንደ ተቀበረ፥ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ እንዳለ በግልጥ ልንገራችሁ።
ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር፤ እስጢፋኖስ በሞተበት ቀን በኢየሩሳሌም በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያት በቀር አማኞች ሁሉ ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ ምድር ተበተኑ።