Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 2:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 “ወንድሞቼ ሆይ! ከቀድሞ አባቶች አንዱ የሆነው ዳዊት እንደ ሞተና እንደ ተቀበረ፥ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ እንዳለ በግልጥ ልንገራችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “ወንድሞች ሆይ፤ ከቀደምት አባቶች ዳዊት ሞቶ እንደ ተቀበረ፣ መቃብሩም እስከ ዛሬ ድረስ በመካከላችን እንደሚገኝ በድፍረት መናገር እችላለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ወንድሞች ሆይ! ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 “እና​ንተ ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስለ አባ​ቶች አለቃ ስለ ዳዊት ነገር እንደ ሞተ እንደ ተቀ​በ​ረም፥ መቃ​ብ​ሩም እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ እንደ አለ ገልጬ እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ትፈ​ቅ​ዱ​ል​ኛ​ላ​ች​ሁን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 2:29
8 Referencias Cruzadas  

ዳዊት ሞተ፤ የእርሱ ከተማ በሆነችው በኢየሩሳሌምም ተቀበረ፤


የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የነበረው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር (ከዳዊት መቃብር ትይዩ ጀምሮ)፥ እስከ ኩሬ፤ እስከ ጀግኖች ሰፈር ድረስ ያለውን ክፍል ሠራ።


ነገር ግን ዳዊት በሕይወቱ ዘመን አገልግሎቱን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከፈጸመ በኋላ ሞቶአል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮአል፤ መበስበስም ደርሶበታል።


የሕይወትን መንገድ አስታወቅኸኝ፤ ከእኔም ጋር በመሆንህ ደስታዬ ፍጹም ይሆናል።’


ይህም እውነት መሆኑን የካህናት አለቃውና የሽማግሌዎች ሸንጎ በሙሉ ይመሰክሩልኛል። እንዲያውም በደማስቆ ያሉትን እነዚህን ሰዎች አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣትና ለማስቀጣት የሚያስችለኝን በደማስቆ ወደሚገኙት ወገኖቻቸው የጻፉትን ደብዳቤ የተቀበልኩት ከእነርሱ ነው።


በፊቱ በግልጥ የተናገርኩት ንጉሥ ይህን ነገር ያውቃል። ይህም በስውር ያልተደረገ ስለ ሆነ ንጉሡ እንደሚረዳው እርግጠኛ ነኝ።


ይህ ሰው እንዴት ታላቅ እንደ ሆነ ተመልከቱ፤ የነገድ አባት የሆነው አብርሃም እንኳ በምርኮ ካገኘው ነገር ዐሥራት አውጥቶ ሰጠው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos