ሐዋርያት ሥራ 13:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕግና የነቢያት መጻሕፍት ከተነበቡ በኋላ የምኲራቡ አለቆች “ወንድሞች ሆይ፥ ሕዝቡን የሚያጽናና የምክር ቃል ካላችሁ ተናገሩ” ብለው ወደነጳውሎስ ሰው ላኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕግና የነቢያት መጻሕፍት ከተነበቡ በኋላ፣ የምኵራብ አለቆች፣ “ወንድሞች ሆይ፤ ሕዝቡን የሚመክር ቃል ካላችሁ ተናገሩ” ሲሉ ላኩባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕግና ነቢያትም ከተነበቡ በኋላ የምኵራቡ አለቆች “ወንድሞች ሆይ! ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ፤” ብለው ላኩባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦሪትንና ነቢያትን ካነበቡ በኋላም የምኵራቡ አለቆች፥ “እናንተ ወንድሞቻችን ሆይ፥ ለሕዝብ ሊነገር የሚገባው የምክር ቃል እንደ አላችሁ ተናገሩ” ብለው ላኩባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕግና ነቢያትም ከተነበቡ በኋላ የምኵራቡ አለቆች፦ “ወንድሞች ሆይ፥ ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ” ብለው ላኩባቸው። |
ኢየሱስ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “የሕግና የነቢያት መጻሕፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ ሲነገሩ ቈይተው ነበር፤ ከዚያም ወዲህ የሚነገረው የእግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች ቃል ነው፤ እያንዳንዱም ሰው ወደዚያች መንግሥት ለመግባት ብርቱ ጥረት ያደርጋል።
“ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት ሰዎች መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ፥ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል መፈጸም ነበረበት።
በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው ኢየሱስ አዳኝ መሆኑን አላወቁም፤ በየሰንበቱም የሚነበቡትን የነቢያት መጻሕፍት ባለማስተዋላቸው በእርሱ ላይ በፈረዱበት ጊዜ ትንቢቱ ተፈጻሚ እንዲሆን አድርገዋል።
ብዙ ክርክር ከተደረገም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞች ሆይ፥ አሕዛብ በእኔ አማካይነት የወንጌልን ቃል ሰምተው እንዲያምኑ ከዚህ በፊት እግዚአብሔር እኔን ከእናንተ መካከል እንደ መረጠኝ ታውቃላችሁ።
“ወንድሞቼ ሆይ! ከቀድሞ አባቶች አንዱ የሆነው ዳዊት እንደ ሞተና እንደ ተቀበረ፥ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ እንዳለ በግልጥ ልንገራችሁ።
የቆጵሮስ ተወላጅ የሆነ፥ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ሐዋርያት “በርናባስ” እያሉ ይጠሩት ነበር፤ ትርጓሜው “የመጽናናት ልጅ” ማለት ነው።
እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞቼና አባቶቼ ሆይ! እስቲ ስሙኝ! አባታችን አብርሃም በካራን ለመኖር ከመሄዱ በፊት ገና በመስጴጦምያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለትና
ስጦታችን መምከር ከሆነ እንምከር፤ ስጦታችን መለገሥ ከሆነ ከልብ እንለግሥ፤ ስጦታችን ማስተዳደር ከሆነ በትጋት እናስተዳድር፤ ስጦታችን ርኅራኄ ማድረግ ከሆነ ይህንኑ በደስታ እናድርግ።
የእነርሱ ልቡና በእርግጥ ደንዝዞአል፤ እስከ ዛሬም ድረስ የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት ሲያነብቡ ልቡናቸው በዚያው መሸፈኛ እንደ ተሸፈነ ነው። ይህም የሚሆነው ያ መሸፈኛ የሚወገደው በክርስቶስ ብቻ ስለ ሆነ ነው።