Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 14:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ትንቢትን የሚናገር ግን ሌላውን ለማነጽ፥ ለማበረታታትና ለማጽናናት ለሰዎች ይናገራል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽ፣ ለማበረታታትና ለማጽናናት ለሰው ይናገራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽ፥ ለማበረታታትና ለማጽናናት ለሰው ይናገራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ትን​ቢ​ትን የሚ​ና​ገር ግን ለማ​ነ​ጽና ለመ​ም​ከር፥ ለማ​ረ​ጋ​ጋ​ትም ለሰው ይና​ገ​ራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር ለማጽናናትም ለሰው ይናገራል።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 14:3
42 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም ዮሐንስ በልዩ ልዩ መንገድ ሕዝቡን እየመከረ መልካሙን ዜና ያበሥር ነበር።


የሕግና የነቢያት መጻሕፍት ከተነበቡ በኋላ የምኲራቡ አለቆች “ወንድሞች ሆይ፥ ሕዝቡን የሚያጽናና የምክር ቃል ካላችሁ ተናገሩ” ብለው ወደነጳውሎስ ሰው ላኩ።


በእነዚያም አገሮች ሁሉ አማኞች በእምነታቸው እንዲጸኑ በማበረታታትና በመምከር “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ብዙ መከራ መቀበል አለብን” እያሉ አስተማሩአቸው።


ይሁዳና ሲላስ ነቢያት ስለ ነበሩ ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጽናኑአቸው፤ አበረታቱአቸውም።


የቆጵሮስ ተወላጅ የሆነ፥ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ሐዋርያት “በርናባስ” እያሉ ይጠሩት ነበር፤ ትርጓሜው “የመጽናናት ልጅ” ማለት ነው።


በይሁዳ፥ በገሊላና በሰማርያ ሁሉ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሰላም አገኘች፤ በረታችም፤ ጌታን እያከበረችና በመንፈስ ቅዱስ እየተጽናናች በቊጥር አደገች።


ስጦታችን መምከር ከሆነ እንምከር፤ ስጦታችን መለገሥ ከሆነ ከልብ እንለግሥ፤ ስጦታችን ማስተዳደር ከሆነ በትጋት እናስተዳድር፤ ስጦታችን ርኅራኄ ማድረግ ከሆነ ይህንኑ በደስታ እናድርግ።


ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችን የምንታነጽበትን ነገር እንከተል።


እያንዳንዳችን ሌላው ሰው በእምነቱ እንዲጠነክር እርሱን የሚጠቅመውንና የሚያስደስተውን ነገር እናድርግ።


ሁሉ ነገር ተፈቅዶአል፤ ነገር ግን ሁሉ ነገር ጠቃሚ አይደለም፤ ሁሉ ነገር ተፈቅዶአል፤ ነገር ግን ሁሉ ነገር የሚያንጽ አይደለም።


እናንተም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች በብርቱ ስለምትሹ በይበልጥ መፈለግ የሚገባችሁ ክርስቲያኖች የሚታነጹባቸው ስጦታዎች እንዲበዙላችሁ ነው።


እርግጥ አንተ ያቀረብከው የምስጋና ጸሎት በጥሩ ሁኔታ ነው፤ ነገር ግን ሌላው ሰው አይታነጽበትም።


ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ምን ማድረግ ይገባል? ለጸሎት በምትሰበሰቡበት ጊዜ ከእናንተ አንዱ የመዘመር ስጦታ አለው፤ ሌላው የማስተማር ስጦታ አለው፤ አንዱ ስውር የሆነውን ነገር የመግለጥ ስጦታ አለው፤ አንዱ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ስጦታ አለው፤ ሌላው የመተርጐም ስጦታ አለው። ታዲያ፥ ይህ ሁሉ ስጦታ ክርስቲያኖችን የሚያንጽ መሆን አለበት።


እያንዳንዱ እንዲማርና እንዲጽናና ሁላችሁም በየተራ የእግዚአብሔርን መልእክት መናገር ትችላላችሁ።


ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋ የሆነ እንደ ሆነ፥ እርግጥ ነው “ሁላችንም ዕውቀት አለን፤” ይሁን እንጂ ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።


እኛ ከእግዚአብሔር በምናገኘው መጽናናት በመከራ ላይ ያሉትን ሁሉ ማጽናናት እንድንችል እግዚአብሔር እኛን በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።


ስለዚህ ይህ ሰው በጣም ከማዘኑ የተነሣ ተስፋ እንዳይቈርጥ ይልቅስ ይቅርታ እንድታደርጉለትና እንድታጽናኑት ይገባል።


ከቶ ከአፋችሁ ክፉ ቃል አይውጣ፤ ነገር ግን ለሚሰሙት ደስ የሚያሰኝና ለማነጽ የሚጠቅም ለሰዎችም አስፈላጊ የሆነውን ቃል ተናገሩ።


ስለዚህ እኛ እንዴት እንደ ሆንን እንድታውቁና እናንተንም እንዲያበረታታችሁ በማለት እርሱን ወደ እናንተ ልኬዋለሁ።


እርሱን ወደ እናንተ የላክሁበት ምክንያት ስለ እኛ ሁኔታ እንዲነግራችሁና ልባችሁንም እንዲያጽናና ነው።


አባት ለልጆቹ እንደሚያደርገው ዐይነት እኛም ለእናንተ ለእያንዳንዳችሁ እንዳደረግንላችሁ ታውቃላችሁ፤


እኛ የመከርናችሁ በስሕተት ወይም በርኩስ ዓላማ ተመርተን አይደለም፤ እናንተን ለማታለል ያደረግነው ምንም ነገር የለም።


ወንድማችንንና የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን፥ የክርስቶስን መልካም ዜና በማብሠር የሥራ ጓደኛችንን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፤ የላክንላችሁም እንዲያጸናችሁና በእምነት እንድትበረቱ እንዲመክራችሁ ነው፤


በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መኖር እንደሚገባችሁ ከእኛ ተምራችኋል፤ አሁንም የምትኖሩት እንዲሁ ነው፤ በጌታ በኢየሱስ ስም የምንለምናችሁና የምንመክራችሁም ከዚህ በፊት ካደረጋችሁት ይበልጥ እንድታደርጉ ነው።


ስለዚህ በዚህ ቃል እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ።


እንደእነዚህ ያሉ ሰዎች ተረጋግተው እንዲሠሩና መተዳደሪያቸውን እንዲያገኙ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛቸዋለን፤ እንመክራቸዋለንም።


ወደ ተረትና መጨረሻ ወደሌለው ወደ ትውልዶች ቈጠራ እንዳይመለሱ እዘዛቸው፤ እነዚህ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉ እንጂ በእምነት ለሚደረገው ለእግዚአብሔር ሥራ አይጠቅሙም።


እኔ እስክመጣ ድረስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለሕዝብ በማንበብ፥ በመስበክና በማስተማር ትጋ።


ጌቶቻቸው አማኞች የሆኑ አገልጋዮች በጌታ ኢየሱስ ወንድሞቻቸው ስለ ሆኑ አይናቁአቸው፤ ይልቅስ ከአገልግሎታቸው ጥቅም የሚያገኙ ጌቶቻቸው አማኞችና የተወደዱ ወንድሞቻቸው ስለ ሆኑ ከበፊት ይበልጥ ያገልግሉአቸው። አንተም ማስተማርና መምከር የሚገባህ ይህን ነው።


ቃሉን ስበክ፤ ቢመችም ባይመችም በማንኛውም ጊዜ ተግተህ ሥራ፤ እያስረዳህ እየገሠጽክና እየመከርክ፥ በትዕግሥትና በማስተማር ትጋ።


እውነተኛውን ትምህርት በማስተማር ለመምከርና ለተቃዋሚዎችም መልስ ለመስጠት እንዲችል በተማረው መሠረት በአስተማማኝ ቃል ይጽና።


እንግዲህ እነዚህን ነገሮች አስተምር፤ በሙሉ ሥልጣንም ምከር፤ ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።


እንዲሁም ጐልማሶች ራሳቸውን በመቈጣጠር እንዲኖሩ ምከራቸው።


አገልጋዮችም ለጌቶቻቸው እንዲታዘዙ፥ በሁሉም ነገር እንዲያስደስቱአቸው፥ ክፉ ቃል እንዳይመልሱላቸው፥


ዘወትር እየተገናኘን እርስ በርሳችን እንበረታታ እንጂ አንዳንዶች ማድረግ እንደ ለመዱት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም የጌታ መምጫ ቀን መቃረቡን እያስታወሳችሁ ይህን ነገር በይበልጥ አድርጉ።


ወንድሞች ሆይ! ይህ የጻፍኩላችሁ መልእክት አጭር ስለ ሆነ ይህን የምክር ቃሌን በትዕግሥት እንድትቀበሉ አጥብቄ እለምናችኋለሁ።


ይልቅስ ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ በየቀኑ ተመካከሩ።


ታማኝ ወንድም ነው ብዬ በማስበው በሲላስ አማካይነት ይህን መልእክት ባጭሩ ጽፌላችኋለሁ፤ የጻፍኩላችሁም ልመክራችሁና ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን ልገልጽላችሁ ብዬ ነው፤ ስለዚህ በዚህ በእግዚአብሔር ጸጋ ጸንታችሁ ቁሙ።


እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ በላይ በተቀደሰው እምነታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ ትጉ፤ በመንፈስ ቅዱስም ኀይል ጸልዩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos