2 ነገሥት 14:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞች በመላክ “እንግዲህ ና ይዋጣልን!” ሲል ለጦርነት አነሣሣው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አሜስያስ የኢዩ የልጅ ልጅ፣ የኢዮአካዝ ልጅ ወደ ሆነው ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ዮአስ፣ “ናና ፊት ለፊት እንጋጠም” ሲል መልእክተኞች ላከበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞች በመላክ “እንግዲህ ና ይዋጣልን!” ሲል ለጦርነት አነሣሣው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜም አሜስያስ፥ “ና እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞችን ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም አሜስያስ “ና፤ እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ፤” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞችን ላከ። |
ዮአስ የፈጸመው ሌላው ነገር ሁሉ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ ላይ ባደረገው ጦርነት የፈጸመው ጀግንነት ጭምር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።
አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቈጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤትሼሜሽ ጦርነት ገጠመው፤
አንተ ከመሰከርክ በኋላ ሌላ ሰው ምስክርነትህ የተሳሳተ መሆኑን የገለጠ እንደሆን ስለምታፍር ስለ አየኸው ነገር ለመመስከር ፈጥነህ ወደ ሸንጎ አትሂድ።
ይህን ሕዝብ የምመራው እኔ በሆንኩ ኖሮ! አቤሜሌክን ወዲያ አስወግደው ነበር፤ ደግሞም ‘ሠራዊትህን በማጠንከር ወጥተህ ተዋጋ!’ ብዬ እነግረው ነበር።”