“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ?
2 ዜና መዋዕል 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኛ አምላክ ከሌሎች አማልክት ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ስለ ሆነ ታላቅ ቤተ መቅደስ ልሠራለት ዐቅጃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አምላካችን ከሌሎች አማልክት ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ስለ ሆነ፣ የምሠራውም ቤተ መቅደስ ታላቅ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላካችንም ከአማልክት ሁሉ በላይ ታላቅ ነውና የምሠራው ቤት ታላቅ የሆነ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን እግዚአብሔርም ከአማልክት ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነውና የምሠራው ቤት ታላቅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችንም ከአማልክት ሁሉ በላይ ታላቅ ነውና የምሠራው ቤት ታላቅ ነው። |
“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ?
ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ይህን አይተው በመደንገጥ ‘እግዚአብሔር ይህን አገርና ይህን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ?’ በማለት ይሳለቁበታል።
ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ ሲል አስታወቀ፤ “እነሆ እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና የሥራ ልምድ የሌለው ነው፤ ይህ የሚሠራው ቤት፥ ቤተ መንግሥት ሳይሆን እግዚአብሔር አምላካችን የሚመለክበት ቤተ መቅደስ ስለ ሆነ መከናወን ያለበት ሥራ እጅግ ከባድ ነው።
“ይህን ስጦታ በፈቃደኛነት መስጠት እንችል ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው? ሁሉ ነገር ከአንተ የተቀበልነው ስጦታ ነው፤ እነሆ የአንተ የነበረውንም መልሰን ሰጥተንሃል፤
ይህ እኔ ልሠራ ያቀድኩት ቤተ መቅደስ ሰፊና እጅግ የተዋበ መሆን ስለሚገባው እኔም ብዙ እንጨት ቈርጠው በማዘጋጀት የአንተን ሰዎች የሚረዱ፥ የእኔን ሰዎች ወደ አንተ ለመላክ ዝግጁ ነኝ።
ልጆቼ ሆይ! በፊቱ ቆማችሁ እንድታገለግሉትና የእርሱ አገልጋዮች እንድትሆኑ፥ መሥዋዕትንም እንድታቀርቡ እግዚአብሔር የመረጣችሁ ስለ ሆነ እንግዲህ ቸልተኞች አትሁኑ።”
“ነገር ግን በእውነት እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሰዎች ጋር ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ፥ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤትማ ምንኛ ያንስ?
“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?
ግብጻውያን በእስራኤል ሕዝብ ላይ ታብየው ያን ያኽል አሳፋሪ ድርጊት በመፈጸማቸው ይህን ሁሉ አስደናቂ ነገር ስላደረገ እነሆ፥ እኔም እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን አሁን ዐወቅሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው?