1 ሳሙኤል 27:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አኪሽ “በዚህ ጊዜ ወረራ ያደረጋችኹት በየት በኩል ነው” ብሎ ሲጠይቀው ዳዊት “እኛ የዘመትነው ከይሁዳ በስተ ደቡብ ባለው ክፍል፥ እንደገናም በይራሕመኤል ነገድ ግዛትና ቄናውያን በሚኖሩበት ግዛት ነው” እያለ ይመልስለት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንኩስም፣ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፣ “የዘመትነው በይሁዳ ደቡብ፣ ወይም በይረሕምኤላውያን ደቡብ፣ ወይም በቄናውያን ደቡብ ላይ ነው” በማለት ይመልስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አኪሽም፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፥ “የዘመትነው በይሁዳ፥ ወይም በይራሕመኤላውያን፥ ወይም በቄናውያን ላይ ነው” እያለ ይመልስለት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንኩስም ዳዊትን፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” አለው፤ ዳዊትም፥ “በይሁዳ ደቡብ፥ በያሴሜጋ ደቡብ፥ በቄኔዛውያን ደቡብ ላይ ዘመትን” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንኩስም፦ ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ? አለ፥ ዳዊትም፦ በይሁዳ ደቡብ፥ በይረሕምኤላውያንም ደቡብ፥ በቄናውያንም ደቡብ ላይ ዘመትን አለ። |
የአቤሴሎም ባለሟሎች ወደዚያ ቤት መጥተው ሴቲቱን “አሒማዓጽና ዮናታን የት ናቸው?” ሲሉ ጠየቁአት። እርስዋም “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ስትል መለሰች። ሰዎቹም ፈልገው ሊያገኙአቸው ስላልቻሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
የሔጽሮን የበኲር ልጅ ይራሕመኤል አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም የመጀመሪያው ራም ቀጥሎም ቡና፥ ኦሬን፥ ኦጼምና አሒያ ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤
የሙሴ ዐማት የነበረው የቄናዊው ዘሮች ከይሁዳ ሕዝብ ጋር በመሆን የተምር ዛፎች ከሞሉባት ከኢያሪኮ ከተማ ተነሥተው፥ በይሁዳ ካለችው ከዐራድ በስተደቡብ ወዳለው ደረቅ ምድር ተጓዙ፤ እዚያም በዐማሌቃውያን መካከል ተቀመጡ።
ቀኔናዊው ሔቤር የሙሴ ዐማት ከነበረው ከሆባብ ልጆች ከቄናውያን ተለየ፤ ወደ ቃዴስ ቀረብ ብሎ በጸእናይም በሚገኘው በታላቁ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተከለ።
“እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ቸርነት ስላደረጋችሁላቸው እናንተን ከአማሌቃውያን ጋር እንዳላጠፋ ከዐማሌቃውያን ተለይታችሁ ሂዱ” ብሎ ሳኦል ለቄናውያን ነገራቸው። እነርሱም ከዐማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ።
ዳዊትም ለካህኑ ለአቢሜሌክ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ እዚህ የመጣሁት የንጉሥ ሳኦልን ተልእኮ ለመፈጸም ነው፤ እኔ ወደዚህ የተላክሁበትን ጉዳይ ለማንም ሰው እንዳልገልጥ ንጉሡ አዞኛል፤ ተከታዮቼንም በአንድ ቦታ እንድንገናኝ አዝዣቸዋለሁ፤
ይህ በዚህ እንዳለ ወዲያውኑ አንድ መልእክተኛ ደርሶ ሳኦልን “ፍልስጥኤማውያን አገሪቱን በመውረር ላይ ናቸውና አሁኑኑ ፈጥነህ ተመልሰህ ና!” አለው።
ዳዊት ወንድንም ሆነ ሴትን ወደ ጋት ሳያመጣ ሁሉንም ገደለ። ይህንንም ያደረገው ዳዊት ይህንንና ይህንን አደረገ ብለው እንዳይነግሩበት ነው። በፍልስጥኤም አገር በኖረበት ዘመን ሁሉ ይህን የማድረግ ልማድ ነበረው።
ዳዊትም “ጌታዬ ምን በደል ሠራሁ? አንተን ማገልገል ከጀመርኩበት ጊዜ አንሥቶ በደል ካልተገኘብኝ ጌታዬና ንጉሤ የሆንከውን አንተን ተከትዬ በመዝመት ጠላቶችህን መውጋት የማልችለው ስለምንድን ነው?” አለው።