በመላው ኤዶም ብዙ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የእርሱ ተገዢዎች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።
1 ነገሥት 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክህ እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማናቸውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ፤ የምታደርገው ሁሉ እንዲከናወንልህ፣ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲሳካልህ፣ በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈው በመንገዶቹ ተመላለስ፣ ሥርዐቶቹንና ትእዛዞቹን፣ ሕጎቹንና ደንቦቹን ጠብቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክህ ጌታ እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማንኛውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደማዝዝህ የምታደርገውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ የተጻፈውን ሥርዐቱንና ትእዛዛቱን፥ ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በርታ፤ ሰውም ሁን፤ የምታደርገውንና የምትሄድበትን ሁሉ ታከናውን ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ ሥርዐቱንና ትእዛዛቱን ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ፥ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ። |
በመላው ኤዶም ብዙ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የእርሱ ተገዢዎች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።
ከዚያም በኋላ በግዛታቸው ውስጥ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ሶርያውያንም ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ገበሩለት፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን እንዲቀዳጅ አደረገው።
ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብ፥ ዕጣንም ያጥን ነበር።
ስለዚህም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሆኖ ስለሚረዳው የሚሠራው ሁሉ በተቃና ሁኔታ ይከናወንለት ነበር፤ ሕዝቅያስ በአሦር ንጉሠ ነገሥት ላይ ዐምፆ ለእርሱ መገዛትን አሻፈረኝ አለ።
አንተ የምታዘውን፥ ትእዛዞችህን ደንቦችህንና ድንጋጌዎችህን ሁሉ እንዲፈጽምና ይህን ሁሉ ዝግጅት ያደረግኹለትን ቤተ መቅደስ እንዲሠራ ለልጄ ለሰሎሞን ከሙሉ ልብ የመነጨ ፈቃደኛነትን ስጠው።”
የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤ ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል።
ስለዚህም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ በመፈጸም ሰባት ቀን ሙሉ ሌሊትና ቀን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ትቈያላችሁ፤ ይህን ባታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ ይህ እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሕግ ነው።”
ከዚህ በኋላ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እስራኤል ሆይ፥ አሁን እንግዲህ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ ለመውረስ ያበቃችሁ ዘንድ የማስተምራችሁን ሕግና ሥርዓት አዳምጣችሁ በሥራ ላይ አውሉት።
“እግዚአብሔር አምላኬ እንድነግራችሁ ያዘዘኝን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አስተምሬአችኋለሁ፤ እርስዋን ለመውረስ በምትገቡባት ምድር ስትኖሩ እነዚህን ትእዛዞች አክብሩ።
የቱንስ ያኽል ታላቅ ቢሆን ዛሬ እኔ በፊታችሁ ቆሜ እንደማስተምራችሁ እንደዚህ ያለ ትክክልና ቅን የሆነ ሕግና ሥርዓት ያለው ሕዝብ የት ይገኛል?
ሙሴም የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ዛሬ የምነግራችሁን ሕግና ሥርዓት ሁሉ አድምጡ፤ በጥንቃቄም አጥንታችሁ እነዚህን ትእዛዞች ጠብቁ።
ሙሴ የሰጣችሁን ሕግና ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ ይኸውም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ውደዱ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ ትእዛዙንም ጠብቁ፤ ለእርሱም ታማኞች ሆናችሁ በሙሉ ልባችሁ፥ በፍጹም ሐሳባችሁ አገልግሉት።”
ስለዚህም በኦሪት ሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዞች ሁሉ ለመጠበቅ ብርቱ ጥንቃቄ አድርጉ፤ ከእነርሱም ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ አትበሉ።
የፍልስጥኤማውያን ወታደሮች በየጊዜው እየመጡ ጦርነት ያደርጉ ነበር፤ ይሁን እንጂ በማናቸውም ጦርነት ሁሉ ከሳኦል የጦር መኰንኖች ይበልጥ ድል የሚሳካለት ለዳዊት ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ዳዊት እጅግ ዝነኛ ሆነ።
ሳኦል በትእዛዝ በሚያዘምትበት ቦታ ሁሉ የዳዊት ተልእኮ የተሳካ ሆነ፤ ስለዚህም ሳኦል በጦር ሠራዊቱ ውስጥ የመኰንንነት ማዕርግ እንዲኖረው አደረገ፤ ይህም የሳኦልን የጦር መኰንኖችና ወታደሮችን ሁሉ አስደሰተ።