138 ሕግህ በፍጹም እውነትና ትክክል ነው።
138 ምስክርነትህን በጽድቅ አዘዝህ፤ እጅግ አስተማማኝም ነው።
138 ምስክርህን በጽድቅ አዘዝህ፥ እጅግም ቅን ነው።
ሥርዓትህ ዘወትር ትክክል ነው፤ በሕይወት ለመኖር እንድችል ማስተዋልን ስጠኝ።
ትእዛዞችህ ሁሉ የጸኑ ናቸው፤ ያለ ምክንያት ስለሚያሳድዱኝ እርዳኝ!
ከግብጽ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤላውያን ያስተላለፈላቸው ድንጋጌዎች፥ ሕጎችና ደንቦች ከዚህ በላይ ያሉት ናቸው፤
የቱንስ ያኽል ታላቅ ቢሆን ዛሬ እኔ በፊታችሁ ቆሜ እንደማስተምራችሁ እንደዚህ ያለ ትክክልና ቅን የሆነ ሕግና ሥርዓት ያለው ሕዝብ የት ይገኛል?