አምላኬ ሆይ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ በክብሬም እዘምራለሁ።
በገናና መሰንቆም ተነሡ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
በገናዬና መሰንቆዬም ተነሡ፤ እኔም በማለዳ እነሣለሁ።
የዐመፀኛ አፍና የኀጢአተኛ አፍ በላዬ ተላቅቀዋልና። በሽንገላ አንደበትም በላዬ ተናገሩ፤
ፍጥረቶቹ ሁሉ በግዛቱ ስፍራ ሁሉ፥ ጌታን ባርኩ። ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ።
ጌታን በመሰንቆ አመስግኑት፥ ዐሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት።
ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።
እኔ ችግረኛና ቁስለኛ ነኝ፥ አቤቱ፥ መድኃኒትህ ያቁመኝ።
ለኃይላችን ለእግዚአብሔር በደስታ ዘምሩ፥ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ።
ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፥ ባራቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ።