ዘሌዋውያን 18:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱም ረከሰች፤ ስለዚህ ስለ በደልዋ እቀጣታለሁ፥ ምድሪቱም የሚኖሩባትን ሰዎች አንቅራ ትተፋቸዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱም ሳትቀር ረከሰች፤ እኔም ስለ ኀጢአቷ ቀጣኋት፤ ስለዚህ የሚኖሩባትን ሰዎች ተፋቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሪቱ ረከሰች፤ በበደልዋ ምክንያት ቀጣኋት፤ እርስዋም የሚኖሩባትን ሰዎች አንቅራ ተፋቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱም ረከሰች፤ ስለዚህ ኀጢአቷን በእርስዋ ላይ እመልሳለሁ፤ ምድሪቱም የሚኖሩባትን ሰዎች ትተፋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱም ረከሰች፤ ስለዚህ ኃጢአትዋን በእርስዋ ላይ እመልሳለሁ፥ ምድሪቱም የሚኖሩባትን ሰዎች ትተፋለች። |
በአገልጋዮችህ በነቢያት እንዲህ ስትል ያዘዝኸውን ‘ልትወርሱአት የምትገቡባት ምድር፥ በምድሩ ሕዝቦች ርኩሰት የረከሰች ምድር ናት፤ ከዳር እስከ ዳርም በርኩሰታቸውና በአጸያፊ ተግባራቸው ተሞልታለች።
በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቁጣውን ሊያመጣባቸው፥ እነሆ፥ ጌታ ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ያፈሰሰችውን ደም ትገልጣለች፥ የተገደሉትንም ከእንግዲህ ወዲህ አትሸሽግም።
ጌታ ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “በእውነት መቅበዝበዝን ወድደዋል፥ እግራቸውንም አልከለከሉም፤ ስለዚህ ጌታ በእነርሱ ደስ አይሰኝም፥ በደላቸውንም አሁን ያስታውሳል ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።”
ምድሬንም በተጠሉ ጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኃጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
ፍሬዋንና በረከትዋንም እንድትበሉ ወደ ፍሬያማ ምድር አስገባኋችሁ፤ ነገር ግን በገባችሁ ጊዜ ምድሬን አረከሳችሁ፥ ርስቴንም የተጠላች አደረጋችሁ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ ሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በጎቼን በትናችኋል አባርራችኋቸዋልም አልጐበኛችኋቸውምም፤ እነሆ፥ ስለ ክፉ ሥራችሁ እጐበኛችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።
የተመረጠውን መሥዋዕቴን ያቀርባሉ፥ ሥጋንም ያርዳሉ፥ ይበላሉም፤ ጌታ ግን በእነርሱ ደስ አይሰኝም፤ በደላቸውን አሁን ያስታውሳል፥ ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።
ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ፤ እናንተም የአገሩም ተወላጅ በእናንተም መካከል የሚኖር እንግዳ ርኩሰት ከሆኑት ከእነዚህ ማናቸውንም ነገር አታድርጉ፤
እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነውና፥ ከእነዚህ አጸያፊ ልምዶች የተነሣም ጌታ እግዚአብሔር እነዚያን አሕዛብ ከፊትህ ያባርራቸዋል።
በድኑን በዕንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድረው፤ ምክንያቱም በዕንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፤ አምላክህ ጌታ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ በዚያኑ ዕለት ቅበረው።”
ምድራቸውን እንድትወርስ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፥ ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ ሕዝቦች ኃጢአት ምክንያትና፥ ለአባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብ፥ ጌታ የማለላቸውን ቃል እንዲፈጸም ነው።