ሰቈቃወ 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛይ። ኢየሩሳሌም በጭንቀትዋና በመከራዋ ወራት ከጥንት ጀምሮ የነበረላትን የከበረን ነገር ሁሉ አሰበች፥ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት በመፍረስዋም ሳቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተጨነቀችባቸውና በተንከራተተችባቸው ቀናት፣ ኢየሩሳሌም በጥንት ዘመን የነበራትን፣ ሀብት ሁሉ ታስባለች፤ ሕዝቦቿ በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፣ የረዳት ማንም አልነበረም፤ ጠላቶቿ ተመለከቷት፤ በመፈራረሷም ሣቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሩሳሌም ሕዝብ በቀድሞ ጊዜ የነበሩአቸውን የከበሩ ነገሮች በችግራቸውና በጭንቀታቸው ቀን ያስታውሳሉ፤ እነርሱም በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፥ አንድም ረዳት ባልነበራቸው ጊዜ፥ ጠላቶቻቸው የከተማቸውን ውድቀት ተመልክተው ተሳለቁባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛይ። ኢየሩሳሌም ቀድሞ ወድዳ በሠራችው ሥራ ሁሉ የመከራዋን ወራት አሰበች፤ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ፥ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት፤ በመፍረስዋም ሳቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛይ። ኢየሩሳሌም በጭንቀትዋና በመከራዋ ወራት ከጥንት ጀምሮ የነበረላትን የከበረን ነገር ሁሉ አሰበች፥ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት በመፍረስዋም ሳቁ። |
“የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔን እንድትጠይቁኝ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ ‘እነሆ፥ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል።
ለአሞንም ልጆች እንዲህ በላቸው፦ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፥ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት ተማርከው በተወሰዱ ጊዜ እሰይ ብለሻልና፤
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ምድር ላይ በውስጥሽ ባለው ንቀት ሁሉ ደስ ብሎሽ በእጅሽ አጨብጭበሻልና፥ በእግርሽም አሸብሽበሻልና፥
እናታቸው አመንዝራለች፤ የፀነሰቻቸውም እርሷ አሳፋሪ ነገር አድርጋለች፤ ምክንያቱም፦ እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ጥጤንና የተልባ እግሬን፥ ዘይቴንና መጠጤን ከሚሰጡኝ ከውሽሞቼ በኋላ እሄዳለሁ፥ ብላለችና።
አብርሃም ግን ‘ልጄ ሆይ! አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም ነገሮችህን እንደተቀበልህ አስብ፤ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል፤ አንተም ትሠቃያለህ።