Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሰቈቃወ 1:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የኢየሩሳሌም ሕዝብ በቀድሞ ጊዜ የነበሩአቸውን የከበሩ ነገሮች በችግራቸውና በጭንቀታቸው ቀን ያስታውሳሉ፤ እነርሱም በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፥ አንድም ረዳት ባልነበራቸው ጊዜ፥ ጠላቶቻቸው የከተማቸውን ውድቀት ተመልክተው ተሳለቁባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 በተጨነቀችባቸውና በተንከራተተችባቸው ቀናት፣ ኢየሩሳሌም በጥንት ዘመን የነበራትን፣ ሀብት ሁሉ ታስባለች፤ ሕዝቦቿ በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፣ የረዳት ማንም አልነበረም፤ ጠላቶቿ ተመለከቷት፤ በመፈራረሷም ሣቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ዛይ። ኢየሩሳሌም በጭንቀትዋና በመከራዋ ወራት ከጥንት ጀምሮ የነበረላትን የከበረን ነገር ሁሉ አሰበች፥ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት በመፍረስዋም ሳቁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ዛይ። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀድሞ ወድዳ በሠ​ራ​ችው ሥራ ሁሉ የመ​ከ​ራ​ዋን ወራት አሰ​በች፤ ሕዝ​ብዋ በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች እጅ በወ​ደቀ ጊዜ፥ የሚ​ረ​ዳ​ትም በሌ​ላት ጊዜ፥ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች አዩ​አት፤ በመ​ፍ​ረ​ስ​ዋም ሳቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ዛይ። ኢየሩሳሌም በጭንቀትዋና በመከራዋ ወራት ከጥንት ጀምሮ የነበረላትን የከበረን ነገር ሁሉ አሰበች፥ ሕዝብዋ በአስጨናቂዎች እጅ በወደቀ ጊዜ የሚረዳትም በሌላት ጊዜ፥ አስጨናቂዎች አዩአት በመፍረስዋም ሳቁ።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 1:7
23 Referencias Cruzadas  

“የአሁኑ ኑሮዬ ቀድሞ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ እንደ ነበረው ጊዜ ቢሆንልኝ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር!


እኔ እፊት እፊት ሆኜ እየመራሁ ከብዙ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄድ ነበር፤ በዓል የሚያደርጉት ሰዎችም በመዝሙርና በእልልታ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ በዚህ ዐይነት ያለፈውን ጊዜ ሳስታውስ ልቤ በሐዘን ይሰበራል።


ስለ እግዚአብሔር በማስብበት ጊዜ እተክዛለሁ፤ በጥሞና ሳሰላስል መንፈሴ ይዝላል።


ለጐረቤቶቻችን መዘባበቻ፥ በዙሪያችን ላሉ መሳቂያና መሳለቂያ ሆነናል።


የተቀደሱ ከተሞችህ በረሓ ሆነዋል፤ ጽዮን በረሓ ኢየሩሳሌምም ባድማ ሆነዋል።


የቀድሞ አባቶቻችን አንተን ሲያመሰግኑበት የነበረ፥ ቅዱስና ውብ የሆነው ቤተ መቅደስህ በእሳት ጋይቶአል፤ የሚያስደስቱ ነገሮች ሁሉ ፈራርሰዋል።


ሞአብ ሆይ! እስራኤል ከሌቦች ጋር የተያዘች ባትሆንም እንኳ አንቺ እርስዋን መሳለቂያ አድርገሽ ስለ እርስዋ በተናገርሽ ቊጥር ራስሽን ትነቀንቂ ነበር።


በከንቱ ረዳት በመጠበቅ ዐይናችን ደከመ ሊታደግ ከማይችል ሕዝብ በጒጒት ርዳታ ጠበቅን።


ለአሞናውያን፥ ጌታ እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ በላቸው፦ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቤተ መቅደሴ እንዲረክስ በተደረገ ጊዜ፥ የእስራኤል ምድር ባድማ በሆነ ጊዜ፥ የይሁዳ ሕዝብ ተማርኮ በተወሰደ ጊዜ እሰይ ብላችኋል።


“ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ በእጃችሁ በማጨብጨብና በእግራችሁም በመርገጥ የእስራኤልንም ምድር በንቀት ተመልክታችኋት ነበር።


ፍቅረኞችዋን ተከትላ ትሄዳለች፤ ነገር ግን ልትደርስባቸው አትችልም፤ ትፈልጋቸዋለች፤ ነገር ግን አታገኛቸውም፤ ከዚህ በኋላ “ከአሁኑ ኑሮዬ ይልቅ የዱሮው ይሻለኛል፤ ስለዚህ ወደ ቀድሞው ባሌ እሄዳለሁ” ትላለች።


አሁን ግን ብዙ ሕዝቦች በእናንተ ላይ ተሰብስበው እንዲህ ይላሉ፦ “ኢየሩሳሌም ትርከስ! እኛም መፍረስዋን እንይ!”


በዚህ ጊዜ ልጁ ስሕተቱን ተገንዝቦ እንዲህ ሲል አሰበ፤ ‘በአባቴ ቤት ተቀጥረው የሚሠሩ አገልጋዮች እንጀራ እስኪጠግቡ በልተው የሚተርፋቸው ስንት ናቸው! እኔ ግን እዚህ በረሀብ መሞቴ ነው፤


“አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በምድራዊ ሕይወትህ ዘመን ብዙ መልካም ነገር አግኝተህ እንደ ተደሰትህ አስታውስ፤ አልዓዛር ግን በችግር ላይ ነበር፤ ስለዚህ አሁን እርሱ እዚህ ሲደሰት አንተ ትሠቃያለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos