ኢዮብ 34:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት በጠፋ፣ ሰውም ወደ ዐፈር በተመለሰ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ዘር ሁሉ በአንድነት በጠፋ ነበር፤ ወደ ዐፈርም በተመለሰ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይሞታል፥ ሟችም ሁሉ ወደ ተፈጠረበት መሬት ይመለሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል። |
እኛ ሁላችን መሞታችን አይቀሬ ነው፤ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር የተሰደደ ሰው በስደት በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።