La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 23:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፥ እንደዚህ ያሉ ብዙ ብያኔዎች እንዳሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤ ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በእኔ ላይ ያቀደውን ሁሉ ይፈጽመዋል፤ ይህንንም የሚመስሉ ብዙ ዕቅዶች አሉት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚ​ህም እኔ ስለ እርሱ ቸኰ​ልሁ፤ በተ​ገ​ሠ​ጽ​ሁም ጊዜ አሰ​ብ​ሁት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእኔ ላይ የተወሰነውን ይፈጽማል፥ እንደዚህም ያለ ብዙ ነገር በእርሱ ዘንድ አለ።

Ver Capítulo



ኢዮብ 23:14
12 Referencias Cruzadas  

እነዚህንም ነገሮች በልብህ ውስጥ ሰወርህ፥ ይህ ሁሉ በአሳብህ እንዳለ አውቃለሁ።


እርሱ ግን የሚተካከለው የለውም፥ ማንስ ውሳኔውን ያስቀይረዋል? የወደደውንም ያደርጋል።


ስለዚህ በፊቱ ደነገጥሁ፥ ባሰብሁም መጠን ፈራሁት።


እንዲሁ ዕጣዬ የከንቱ ወራት ሆነብኝ፥ የድካምም ሌሊት ተወሰነችልኝ።


የነጐድጓድህ ድምፅ በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነበረ፥ መብረቆች ለዓለም አበሩ፥ ምድር ተናወጠች ተንቀጠቀጠችም።


ደመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፥ ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።


የጌታ ድምፅ ከተማይቱን ይጠራታል፤ ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፤ ወገን ሆይ፥ ያዘጋጀው ማን እንደሆነ ስሙ።


የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው! መንገዱም የማይታወቅ ነው።


በዚህ መከራ ማንም እንዳይናወጥ፥ ለዚህ እንደ ተሾምን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።


እግዚአብሔር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መዳንን እንድናገኝ እንጂ ለቁጣ እንድንሆን አስቀድሞ አልመረጠንም።


ደግሞም፦ “ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ የሚጥላቸውም ዓለት ሆነ፤” የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።