በምክራቸው፥ ነፍሴ፥ አትግባ፥ ከጉባኤአቸውም ጋር፥ ክብሬ፥ አትተባበር፥ በቁጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነክሰዋልና።
ኢዮብ 21:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ ሀብታቸው በእጃቸው ውስጥ አይደለምን? የክፉዎች ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁንና ብልጽግናቸው በእጃቸው አይደለም፤ ከኀጢአተኞች ምክር እርቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የሚሉት በእጃቸው ያለው ሀብት ሁሉ በራሳቸው ጥረት የተገኘ ስለሚመስላቸው ነው፤ እኔ ግን የክፉ ሰዎችን ሐሳብ አልቀበልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ፥ በጎነታቸው በእጃቸው ውስጥ አለች፤ የኃጥኣንን ሥራ አይመለከትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ሀብታቸው በእጃቸው ውስጥ አይደለምን? የኃጥአን ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት። |
በምክራቸው፥ ነፍሴ፥ አትግባ፥ ከጉባኤአቸውም ጋር፥ ክብሬ፥ አትተባበር፥ በቁጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነክሰዋልና።
መንፈስን ለማገድ በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ላይ ሥልጣን የለውም፥ በጦርነትም ውስጥ መሰናበቻ የለም፥ ክፋትም ሠሪውን አያድነውም።
አብርሃም ግን ‘ልጄ ሆይ! አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም ነገሮችህን እንደተቀበልህ አስብ፤ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል፤ አንተም ትሠቃያለህ።