Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 1:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እንዲህም አለ፦ “ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፥ ጌታ ሰጠ፥ ጌታ ወሰደ፥ የጌታ ስም የተባረከ ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እንዲህም አለ፤ “ዕራቍቴን ከእናቴ ማሕፀን ወጣሁ፤ ዕራቍቴንም እሄዳለሁ። እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ተወለድኩ፤ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!” አለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ራቁ​ቴን ወጥ​ቻ​ለሁ፥ ራቁ​ቴ​ንም ወደ ምድር እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጠ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነሣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ብ​ሔር ስም የተ​ባ​ረከ ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እንዲህም አለ፦ ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፥ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፥ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 1:21
35 Referencias Cruzadas  

ይህም ደግሞ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ነው፥ እንደመጣ እንዲሁ ይሄዳል፥ ድካሙም ለነፋስ ከሆነ ጥቅሙ ምንድነው?


ወደዚህ ዓለም ምንም ይዘን አልመጣንምና፥ ከዚህም ዓለም ይዘነው የምንሄደው ምንም ነገር የለም፤


በሁሉ ነገር አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።


መልካም ስጦታ ሁሉ፥ ፍጹምም በረከት ሁሉ፥ እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከላይ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


እርሱ ግን፦ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፥ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን?” አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም።


ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።


ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ አበለጽጋለሁ፤ አደኸያለሁ፤ ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ ጌታ ነኝ።


የሰው ሀብት የቤቱም ክብር በበዛ ጊዜ አትፍራ፥


ጌታ ድሀ ያደርጋል፤ ሀብታምም ያደርጋል፤ ያዋርዳል ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።


ከልዑል አፍ ክፉና መልካም ነገር አይወጣምን?


አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።


“ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በግንባርህ ላብ እንጀራን ትበላለህ፥ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።”


የራሴ በሆነ ነገር ላይ የወደድሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንኩ ትመቀኛለህን?


ከመተላለፌ ሁሉ አድነኝ፥ የሞኞች መሳለቂያ አታድርገኝ።


ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ለመሄድ ያልወደዱት፥ ለሕጉም ያልታዘዙለት ጌታ እርሱ አይደለምን?


ባሳደደው በአቤሜሌክ ፊት መልኩን በለወጠ ጊዜ በሄደም ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።


ነገር ግን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ዳስስ፥ በእውነት በፊትህ ይሰድብሃል።”


ስለዚህ ሳሙኤል ምንም ነገር ሳይደብቅ ሁሉንም ነገረው። ዔሊም፥ “እርሱ ጌታ ነው፤ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ።


አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ፥ አትቈርቈሩም፥ እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት ልኮኛልና።


ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ቢነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ጌታ ካላደረገው በቀር በከተማ ላይ ክፉ ነገር ይሆናልን?


ስለዚህ ጌታን በምሥራቅ፥ የእስራኤልንም አምላክ የጌታንም ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ።


እግዚአብሔር በልቡ ደስታን እስካኖረ ድረስ፥ እርሱ የሕይወቱን ዘመን እጅግም አያስብም።


ንጉሥ ሕዝቅያስም በተለይ በእርሱ ዘመን በሰላም የመኖር ዋስትና እንዳለ ስለ ተረዳ “ከእግዚአብሔር ተልከህ የተናገርከኝ ቃል መልካም ነው” ሲል መለሰ።


ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ጌታ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት ጌታ ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።


ጌታ ምናልባት በዚህ ቀን መከራዬን አይቶ ስለ እርግማኑ መልካም ይመልስልኛል” አላቸው።


ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፦ በውኑ እኔ የሆድን ፍሬ በነሣሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? አላት።


በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው።


በሙላት ወጣሁ፥ ጌታም ባዶዬን መለሰኝ፤ ጌታ በእኔ ላይ ሰቆቃን ሲያደርስ፥ ሁሉን የሚችል አምላክ አስጨንቆኛልና፥ ናዖሚ ብላችሁ ለምን ትጠሩኛላችሁ?” አለቻቸው።


ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ሊያደርጋቸው፥ የክብርንም ዙፋን ሊያወርሳቸው፥ እርሱ ድኾችን ከትቢያ፥ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ የምድር መሠረቶች የጌታ ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አኖረ።


ሌዋውያኑ ኢያሱ፥ ቃድምኤል፥ ባኒ፥ ሐሻብንያ፥ ሼሬብያ፥ ሆዲያ፥ ሽባንያ፥ ፕታሕያ እንዲህ አሉ፦ “ቁሙ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ጌታ አምላካችሁን ባርኩ። ከበረከትና ከምስጋና ሁሉ በላይ ከፍ ያለው የክብርህን ስም ይባርኩ።


እነሆ፥ ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?”


ጌታን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር ከአፌ አይለይም።


ከእናቱ ሆድ ራቁቱን እንደ ወጣ እንዲሁ እንደ መጣው ይመለሳል፥ ከጥረቱም በእጁ ሊወስደው የሚችለው ምንም ነገር የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios