ኢዮብ 18:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥ በሜዳም ስም አይቀርለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መታሰቢያው ከምድር ገጽ ይጠፋል፤ ስሙም በአገር አይነሣም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር ላይ የሚያስታውሰው አይኖርም። ዝናውም ከምድር ይጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መታሰቢያውም ከምድር ይጠፋል፤ በምድርም ስም አይቀርለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥ በሜዳም ስም አይቀርለትም። |
እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፤ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፤ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል፤ አጥፍተሃቸውማል፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ እንዳልነበር አድርገሃል።
ጌታ ከእንግዲህ ወዲህ በስምህ እንዳይዘራ ስለ አንተ አዝዞአል፤ ከአምላኮችህ ቤት ጣዖትንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል አጠፋለሁ። አንተም የማትረባ ነህና መቃብርህን እምሳለሁ።